የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደንበኞች ቁጥሩ ከ5.46 ሚሊየን በላይ መድረሱን ገለፀ

Date:

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የ2018 አ.ም የስድስት ወር የዕቅድ አፈፃፀሙን በትናንትናዉ እለት ለመገናኛ ብዙሃን ይፋ አድርጓል፡፡

ባለፉት 6 ወራት ኤሌክትሪክ የተገናኘላቸው ደንበኞች ጨምሮ አጠቃላይ  የደንበኞች ቁጥር 5.46 ሚሊዮን በላይ መሻገሩን ገልጿል።

1.1 ሚሊዮን የኢነርጂ ቆጣሪዎችን ቤት ለቤት ለመመርመር አቅዶ  1.29 ሚሊዮን መመርመር እንደቻለ የገለፀዉ አገልግሎቱ በምርመራው 39 ሺህ 704 ግኝቶች ተገኝተው የማስተካከያ እርምጃ እንደተወሰደም ተገልጿል።

መግለጫውን የሰጡት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢ/ር ጌቱ ገረመዉ፤ከኢነርጂ ሽያጭ ከተሰበሰበው 34.3 ቢሊዮን ብር ገቢ ውስጥ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል 20.5 ቢሊዮን ብር ለኢነርጂ ግዥ ክፍያ መፈፀሙን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የተጠያቂነትን ስርዓት ለማስፈን ባከናወነው ሥራ 6መቶ51 አመራርና ሠራተኞች ላይ እርምጃ መውሰዱን ከመድረኩ ሰምተናል።

የኤሌክትሪክ ኃይል ስርቆት የፈፀሙ 18 ግለሰቦች ላይ ክስ ተመስርቶ 2ሺህ ብር መቀጮ እና 2.95 ሚሊየን ብር እንዲከፍሉ ስለመደረጉ በተገለፀበት መድረክ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ስርቆት እና ውድመት ባደረሱ 14 ግለሰቦች ላይ ክስ ተመስርቶ ከ2 ሺህ ብር መቀጮ ጀምሮ እስከ 10 ዓመት ፅኑ እስራት ድረስ እንዲቀጡ በፍርድ ቤት ስለመወሰኑም ተገልጿል።

በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወር ከኢነርጂ ሽያጭ፣ ከአዲስ ደንበኛ መስተንግዶ፣ ከማያገለገሉ ንብረቶች ሽያጭና ከልዩ ልዩ ገቢ 52.26 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ ተችሏል ተብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...

የተጀመሩ የትምህርት ሪፎርሞችን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም በቁርጠኝነት መስራት ይገባል

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ...

የአዉሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የቡና ገበያ መዳረሻዎች እየፈለገ ነዉ

በፈረንጆቹ 2023 የፀደቀው የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ ህግ ምርቶች...