ከሪፐብሊካኖቹ የተሰነዘረ ቁጣ ለዶናልድ ትራምፕ

Date:

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቀድሞ መሪ ባራክ ኦባማና ባለቤታቸው ሚሼል ኦባማ ላይ ቀልድ አዘል የዘረኝነት ተንቀሳቃሽ ምስል ማጋራታቸው ቁጣን ቀስቅሷል፡፡

ዶናልድ ትራምፕ በኤክስ ትስስር ገጻቸው ባራክ ኦባማን ጨምሮ ሌሎች የቀድሞ መሪዎች በዝንጀሮና ሌሎችም እንስሳት በመመሰል ተንቀሳቃሽ ምስል አጋርተዋል፤ተንቀሳቃሽ ምስሉ 62 ሰከንድ እርዝማኔ ያለው ሲሆን The Lion Sleeps Tonight በሚል መጠሪያ በሚታወቀው ሙዚቃ የተቀናበረ ነው፡፡

ተንቀሳቃሽ ምስሉ በአውሮፓውያኑ 2020 በተደረገው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መጭበርበር ክስ አዘል መልእክቶችን ያዘለ መሆኑም ተገልጿል፡፡ ተንቀሳቃሽ ምስሉ በዶናልድ ትራምፕ የትሩዝ ሶሻል ሚዲያ ላይ የተጋራ ሲሆን ለ12 ሰአታት ቆታን አድርጓል፡፡

ኋላ ላይ ምስሉ ይሰረዝ እንጂ ከሪፐብሊካኖች ጭምር ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል፡፡ በሪፐብሊካን ውስጥ ጥቁር ሴናተር የሆነው ቲም ስኮት መሰል ከነጩ ቤተመንግስት የተሰነዘረ የዘረኝነት መልእክት ፈፅሞ አይቼ አላቅም ሲል ተደምጧል፡፡

የትራምፕ ድርጊት አሁንም ተቃውሞዎች የበረቱበት ሲሆን ከነጩ ቤተመንግስት በስህተት የተለቀቀ ነው ሲል ለማስተባበል ተሞክሯል፡፡
ድርጊቱን ተከትሎ ትራምፕ ይቅርታ ይጠይቃሉ ወይ ተብሎ ከሪፖተሮች ለቀረበላቸው ጥያቄ ፈፅሞ ስህተት አልሰራሁም ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

በተንቀሳቃሽ ምስሉ በእንስሳ ተመስለው ከተካተቱ ዲሞክራቶች መካከል የኒዮርክ ተወካይ አሌክሳንድሪያ ኮርቴዝ፣ የኒዮርክ ከንቲባ ዞህራን ማምዳኒ፣የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን ይገኙበታል፡፡

ጆ ባይደን እንዲሁ በተንቀሳቃሽ ምስሉ ሙዝ የሚበላ ዝንጀሮ ሆነው ይታያሉ፤ ባራክ ኦባማ ምስሉን ተከትሎ እስካሁን የሰጡት ምላሽ የለም ሲሉ አልጀዚራና ቢቢሲ ዘግበውታል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...

የተጀመሩ የትምህርት ሪፎርሞችን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም በቁርጠኝነት መስራት ይገባል

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ...

የአዉሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የቡና ገበያ መዳረሻዎች እየፈለገ ነዉ

በፈረንጆቹ 2023 የፀደቀው የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ ህግ ምርቶች...