“በርካታ ጉዳት ደርሶብናል” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

Date:

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሠራተኛ ማኅበሩ ጋር በተገቢው ጊዜ ተወያይቶ ባለመፈራረሙ በርካታ ጉዳት እንደደረሰበት አስታወቀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር በተገቢው ጊዜ ተወያይተውናተደራረድረው ስምምነት ባለመፈራረማቸው ምክንያት ለብዙ ግጭቶችና አለመግባባቶች ምክንያት እንደነበርና ይህም በርካታ ጉዳት ማስከተሉን የአየር መንገዱ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚው ይህን የተናገሩት፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር ላለፉት አሥር ዓመታት ተቋርጦ የነበረውንና 11ኛውን የሕብረት ስምምነት የካቲት 13፣ 2018 ዓ.ም በተፈራረሙበት ወቅት ነው፡፡

በስካይ ላይት ሆቴል በነበረው የፊርማ ሥነ ሥርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ 10ኛው የሕብረት ስምነት ከተፈረመ 13 ዓመታት እንዳስቆጠረና አንድ የሕብረት ስምምነት በተለምዶ በሥራ ላይ የሚውለው ለሶስት ዓመታት ብቻ በመሆኑ አየር መንገዱና ማህበሩ ሲጠቀምበት የኖረው ስምምነት ጊዜው ካለፈ 10 ዓመታት ያህል እንደተቆጠሩ አስረድተዋል፡፡

ይህም በርካታ ጉዳት በድርጅቱ ላይ አድርሷል ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው”በጊዜው ማህበሩና ድርጅቱ ተወያይተንና ተደራረድረን ተገቢውን ስምምነት ባለመፈራረማችን ምክንያት ለብዙ ግጭቶችና አለመግባባቶች፣ በተቋሙ ውስጥ የኢንዱስትሪ ሰላም ለታጣባቸው ወቅቶች ትልቅ ምክንያት ነበር” ብለዋል፡፡ ስምምነቱን ለመፈጸም ለ3 ዓመታት ድርድር ሲካሔድ መቆየቱንም አክለዋል፡፡

አዲሱ 11ኛው የሕብረት ስምምነት በአየር መንገዱ አስተዳደር እና በሠራተኞች መካከል ግልጽ የሆነ መብትና ግዴታን በማስቀመጥ፣ መልካም የሥራ አካባቢን በመፍጠር ለድርጅቱ ውጤታማነት ትልቅ አስተዋጽዖ ይኖረዋል ተብሏል።

በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ  የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ብሩክ ታዬ፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ነቢያ መሐመድ፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዳንኤል ተሬሳ እና ሌሎችም እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...