ለ130ኛው የዓድዋ ድል በዓል አከባበር ሲባል ለትራፊክ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆኑ

Date:

በነገው ዕለት ለሚከበረው 130ኛው የዓድዋ ድል በዓል አከባበር ሲባል ለትራፊክ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሠረት፡-

👉 ከቸርችል ጎዳና በቴዎድሮስ አደባባይ ምኒልክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባንኮ ዲሮማ መብራት፤

👉 ከአራት ኪሎ በራስ መኮንን ወደ ዳግማዊ ምኒልክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ራስ መኮንን ድልድይ፤

👉 ከመነን አካባቢ እና የካቲት 12 ሆስፒታል በአፍንጮ በር ወደ ዳግማዊ ምኒልክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ አፍንጮ በር፤

👉 ከእሪ በከንቱ በኤሌክትሪክ ህንፃ ወደ ዳግማዊ ምኒልክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቀይ ባህር ኮንዶሚኒየም፤

👉 ከአዲሱ ገበያ በሰሜን ሆቴል ወደ ዳግማዊ ምኒልክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሰሜን መብራት፤

👉 ከመርካቶ በአቡነ ጴጥሮስ ወደ ዳግማዊ ምኒልክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደጃዝማች ኃብተ ጊዮርጊስ ድልድይ፤

👉 ከእንቁላል ፋብሪካ በቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ወደ ዳግማዊ ምኒልክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ዮሐንስ መብራት ላይ ነገ የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከንጋቱ 12:00 ጀምሮ ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚደረግ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

በተጠቀሱት ቦታዎች ለአጭርም ሆነ ለረዥም ሰዓት ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፈፅሞ የተከለከለ መሆኑን አሽከርካሪዎች አውቀው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...

የብሔር ፌደራሊዝምን ለማስቀጠል “የቆረጡ” ተመካካሪዎች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 14ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች የአጀንዳ...

“የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው” ፓትርያርኩ

የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው...