“ድርጊቱ በሃይማኖቶች መካከል ግጭት ለመፍጠር የታለመ ነው!” ቋሚ ሲኖዶስ

Date:



በምሥራቅ አርሲ የተፈጸመው የንጹሐን ግድያ ለዘመናት የዘለቀውን የሃይማኖቶች ተከባብሮ የመኖር እሴት ለመናድ የታለመ ነው ሲል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ድርጊቱን በጽኑ አወገዘ።

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በተለያዩ ወረዳዎች በኦርቶዶክሳውያን ላይ እየተፈጸመ ያለው ጥቃት በአዲስ መልክ ቀጥሎ የ21 ንጹሐን ወገኖች ሕይወት በግፍ ማለፉን ቋሚ ሲኖዶስ በመሪር ኃዘን ገልጿል።

ኦርቶዶክሳውያን በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል በነፃነት የመኖርና ሥርዓተ አምልኮ የመፈጸም ሕገ-መንግሥታዊ መብታቸው ሊከበር ይገባል ያለው ቋሚ ሲኖዶሱ፤ የፌዴራልና የክልሉ መንግሥት እርምጃዎች በአፋጣኝ እንዲወስዱ አሳስቧል።

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በተደጋጋሚ እየተፈጸመ ያለው ሞትና መፈናቀልም ኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን በየትኛውም የሀገራችን ክፍል በነጻነት ሠርተው የመኖርና ሥርዓተ አምልኮ የመፈጸም ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን የሚጋፋ በመሆኑ የክልሉና የፌዴራል መንግሥት ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ ተከታትለው አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጡበት ቋሚ ሲኖዶስ በጥብቅ ያሳስባል፣


እንዲሁም ለተፈጸመው ግፍ አፋጣኝ ፍትሕ እንዲሰጥና ገዳዮች በሕግ እንዲጠየቁ እና የዜጎችን ደኅንነትና ንብረት የማስጠበቅ የመንግሥት ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ፤የሀገር ሰላምና የቤተ ክርስቲያን አንድነት ዐቢይ ኮሚቴ ከመንግሥት ጋር በመነጋገር ዘላቂ መፍትሔ እንዲያመጣ ቋሚ ሲኖዶስ አሳስቧል ።

​በመጨረሻም ቋሚ ሲኖዶስ ስለስሙ መከራን ለተቀበሉ” ንጹሐን ዕረፍተ ነፍስን፣ ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን ተመኝቷል።
(#EOTCTV)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለሚገኘው ቅርንጫፉ ተጨማሪ 1.4 ቢሊዮን ሺሊንግ ኢንቨስት አደረገ

የኬንያው የቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ሳፋሪኮም እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም...

በምክክሩ ሕዝበ ውሳኔ የተጠየቀባቸው ጉዳዮች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 15ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች በተጠናቀሩ...

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...