የሩሲያ ጦር በሁሉም የጦር ግንባሮች ወደፊት እየገሰገሰ ነዉ

Date:

​ቫለሪ ጌራሲሞቭ ይህንን መግለጫ የሰጡት የ”ዩግ” የውጊያ ቡድንን ከጎበኙ በኋላ ነው። እንደ አዛዡ ሪፖርት፣ የሩሲያ ጦር በመጋቢት የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሳምንታት ውስጥ 12 ሰፈራዎችን የተቆጣጠረ ሲሆን፣ ከባዱ ውጊያም በክራስኒ ሊማን አቅራቢያ እየተካሄደ ይገኛል።

​ቁልፍ መግለጫዎች፦

🟠  የ”ዩግ” የውጊያ ቡድን 3ተኛ ሠራዊት ወደ ስላቭያንክ እየገሰገሱ ይገኛሉ፡፡

🟠  የሩሲያ ጦር ረዝኒኮቭካ፣ ጎሉቦቭካ እና ካሌኒኪን የተቆጣጠረ ሲሆን፣ ክሪቪ ሉኪ ለመቆጣጠር የሚደረገው ውጊያ አሁንም ቀጥሏል፡፡

🟠  በኮንስታንቲኖቭካ ከተማ ውስጥ ውጊያው የቀጠለ ሲሆን፣ የሩሲያ ጦር ከከተማዋ 60% በላይ የሚሆነውን ተቆጣጥሯል፡፡

🟠  በኦስኮል ወንዝ ምስራቃዊ ዳርቻ በሚገኘው ኖቮሲኖቮ፣ የሩሲያ ጦር ከ85% በላይ የሚሆነውን ቦታ የተቆጣጠረ ሲሆን፣ የዩክሬን ጦር መከበቡ ተዘግቧል፡፡

🟠  የ”ዛፓድ” የውጊያ ቡድን ወደ ክራስኒ ሊማን እየገሰገሰ ሲሆን፣ ከከተማዋ ግማሽ በላይ የሚሆነውን ክፍል ተቆጣጥሯል፡፡

🟠  የ”ዛፓድ” ኃይሎች ድሮቢሼቮ፣ ያሮቫያ እና ሶስኖቮዬን የተቆጣጠሩ ሲሆን፣ አሌክሳንድሮቭካን የመቆጣጠር ስራቸውንም እያጠናቀቁ ነው፡፡

🟠  የ”ሴቨር” የውጊያ ቡድን በሱሚ እና ካርኮቭ ክልሎች ያለውን የደህንነት ቀጣና እያሰፋ ይገኛል። በመጋቢት ወርም አምስት ሰፈራዎችን ተቆጣጥሯል፡፡

🟠  የ”ሴንትር” የውጊያ ቡድን ወደ ዶብሮፖሊዬ እየገፋ ሲሆን፣ በዲኔፕሮፔትሮቭስክ ክልልም እንቅስቃሴውን ቀጥሏል፡፡

🟠  የ”ዲኔፕር” የውጊያ ቡድን ወደ ዛፖሮዝሂዬ አቅጣጫዎች የማጥቃት እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል፤፡፡

🟠  የ”ቮስቶክ” የውጊያ ቡድን በምስራቃዊ ዛፖሮዢዬ ክልል ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ግስጋሴውን የቀጠለ ሲሆን፣ የዩክሬንን የመልሶ ማጥቃት ሙከራዎችንም እየመከተ ይገኛል። የዩክሬን ጦር በየካቲት እና መጋቢት ወራት በዚያ አካባቢ ከ2,500 በላይ ወታደሮችን እና 120 የጦር መሳሪያዎችን አጥቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ምግባረ-መልካሙ ኢትዮጵያዊ

ስለሺ መንገሻ - ከ1934 እስከ 2018 ዓ.ም ሠሎሞን ለማ ገመቹ. ግዮን...

ትራምፕ ለኔታንያሁ ማስጠንቀቂያ ሰጡ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ...

ኤምባሲዎችና የውጭ ባለሀብቶች በ«ፍራንኮ-ቫሉታ» ነዳጅ እንዲያስገቡ ተፈቀደ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ኤምባሲዎች፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና የውጭ...

የሪል ስቴት ኢንቨስትመንት ከዓመታዊ የትርፍ 90 በመቶውን እንዲያከፋፍሉ ሊደረግ ነው

የሪል ስቴት ኢንቨስትመንት ተብለው የሚቋቋሙ ፈንዶች ከዓመት ትርፋቸው ቢያንስ...