ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

Date:

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል ዘርፍ እና ለዲጂታላይዜሽን ፕሮግራም የሚውል የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት መስማማቷን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታውቀዋል፡፡

ይህ ስምምነትየኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎችን የአውቶሜሽን ሥርዓት ለማዘመን እና አዲስ የብሔራዊ ግሪድ መቆጣጠሪያ ማዕከልን ለመገንባት ይውላል ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ የ150 ሜጋ ዋት የጂኦተርማል (የከርሰ ምድር እንፋሎት) ኃይል ለማመንጨት አዲስ የማዕቀፍ ስምምነት ተደርጓል።

የኤሌክትሪክ መቆራረጥን በ 50 በመቶ በመቀነስ ከ4 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የተሻለ የኤሌክትሪክ አቅርቦት እንዲኖር የሚያስችል ስለመሆኑ ተነግሩለታል፡፡

ይህ ደግሞ የካርቦን ልቀትን በ150 ሺህ ቶን በመቀነስ የአካባቢ ጥበቃ ጥረትን ያግዛል።

ስምምነቱ  በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ በአውሮፓ ህብረት እና በፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲዎች (AFD) በትብብር የሚተገበር ሲሆን የሀገሪቱን  የኢነርጂ ዘርፍ ወደ ተሻለ ዲጂታል ከፍታ እንደሚያሸጋግረው ታምኖበታል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በሚኒስትርነት የተሾሙና ከሚኒስትርነት የተነሱት እነማን ናቸዉ ?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለመደመር መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር...

የአዲሱ መንግሥት ምሥረታ

መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም  የኢፌዴሪ የ7ኛው የፓርላማ ዘመን፣...

መልካም አዲስ ዓመት!!

  ግዮን መጽሔት :-   አዲሱን የኢትዮጵያ ዓመት ስንቀበል፣ ለውዷ ኢትዮጵያችንና...

የድሬዳዋ አስተዳደር ተሿሚዎች

4ኛ የስራ ዘመን፣ 1ኛ ዓመት፣ 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን ያካሄደዉ...