በመቐለ ከተማ በወጣቶች ላይ “የግዳጅ አፈሳ” ተጀምሯል

Date:

በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቐለ የጸጥታ ኃይሎች በወጣቶች ላይ “የግዳጅ አፈሳ” ማካሄድ መጀመራቸውን የዓይን እማኞችና የነዋሪዎች መረጃዎች አረጋግጠዋል።

ከዚህ ቀደም በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ሲካሄድ የቆየው ይህ ወታደራዊ ምልመላ አሁን ላይ ወደ ዋና ከተማዋ በይፋ መሸጋገሩ የተገለጸ ሲሆን፣ በከተማው ሰሜን ክፍለ ከተማ ዒላላ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አካባቢ የታፈሱ ወጣቶች በሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶች ተጭነው ሲወሰዱ የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት እየተሰራጩ ይገኛሉ።

ወጣቶቹ በሌሊት የፓትሮል ቅኝትና ከተለያዩ ቦታዎች (ከመስጊድ ጭምር) እየተያዙ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ጣቢያዎች እየተወሰዱ መሆኑን ቤተሰቦቻቸው በምሬትና በለቅሶ ተናግረዋል።

ይህ ድንገተኛ አፈሳ በነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ፍርሃትና ድንጋጤ የፈጠረ ሲሆን፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ነዋሪዎች የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶችን በድንጋይ በመውገር ለማስቆም የሞከሩበት አጋጣሚም ተፈጥሯል።

ከዚህም በተጨማሪ የቀድሞ ተዋጊዎች ወደ ወታደራዊ ምድባቸው እንዲመለሱ በቀበሌ አመራሮች አማካኝነት ከፍተኛ ጫና እና ማስፈራሪያ እየተደረገባቸው ሲሆን፣ ድርጊቱ በሕዝቡ መካከል የነበረውን መተማመን ማሸርሸሩን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

የታፈሱ ወጣቶች ቤተሰቦች ልጆቻቸውን ፍለጋ እስከ 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኘው ደንገላት ወታደራዊ ማሰልጠኛ ቢጓዙም፣ ከልጆቻቸው ጋር እንዳይገናኙና እንዳያነጋግሩ በማሰልጠኛው ጠባቂዎች ተከልክለዋል።

ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች  በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለውን የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ በጽኑ የኮነኑ ሲሆን፣ ምልመላው በአዲግራት፣ በአዲጉደም እና በዛላንበሳ ከተሞች ቀድሞ መጀመሩን ጠቁመዋል።

ይሁን እንጂ ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) እና የፓርቲው ከፍተኛ ሹማምንት የቀረበባቸውን ወቀሳ በማስተባበል፣ “ሊሰነዘር የሚችል ወረራን ለመከላከል መዘጋጀት አለብን አልን እንጂ ምንም ዓይነት የወጣቶች አፈሳ አላካሄድንም” ሲሉ ድርጊቱን ሙሉ በሙሉ ክደዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሁቲዎች በሳዑዲ አውሮፕላን ማረፊያዎች ላይ ጥቃት ለማድረስ ዛቱ

የየመን ሁቲ አማጺያን የሳዑዲ አረቢያን አውሮፕላን ማረፊያዎች እና ሌሎችም...

“የድንቁርና” እና “የታሪክ ፍልሠትን” የሚያስከትል ድርጊት ነው

የቅዱስ ላሊበላ ገዳም ዓለማቀፍ ቅርስ አሥተዳደር ጽሕፈት ቤት፣...

በትምህርት ቤቶች ዙሪያ የትንባሆ መሸጫ ክልከላ ርቀት ወደ 500 ሜትር ከፍ ተደረገ

የአዲስ አበባ ምግብ መድሃኒት ባለስልጣን በትምህርት ቤቶች ዙሪያ የትንባሆ...

አዲሱን የጉምሩክ አዋጅ የባለንብረቶችን ሥጋት ሊፈታ እንደሚገባ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሠሪዎች ፌዴሬሽን፤ አዲሱን የጉምሩክ አዋጅ ለማስፈጸም የሚወጣው...