በሳውዲ ከ1900 በላይ ኢትዮጵያዊ እስረኞች በምህረት ተለቀቁ

Date:

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በ በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ጉዳይ በተመለከተ 1971 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የሳዑዲ ባለሥልጣናት ካደረጉት የንጉሣዊ ምሕረት ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግሥትም እነዚህን ዜጎች ወደ አገራቸው በተከታታይ በረራዎች እየመለሰ የሚገኝ ሲሆን ሚኒስቴሩ ይህንን ሒደት በቆንስላና በሰብዓዊ ጉዳዮች ላይ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ትብብርና የረጅም ዘመን ግንኙነት የሚያንጸባርቅ መሆኑንም አመልክቷል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በውጭ አገር የሚኖሩ የኢትዮጵያውያንን ጥቅሞች፣ መብቶችና ደኅንነት ለመጠበቅ ያሉትን የዲፕሎማሲና የቆንስላ አማራጮች ሁሉ መጠቀሙን እደሚቀጥልም አስታውቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 9 2019 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

-የግዮን እንግዳ አምዳችን :- ‹‹ምንጩና ጸሐፊው በማይታወቅ መረጃ መመራት አደገኛ...

ሸኽ መሃመድ አል አሙዲ ተጨማሪ 40 ሺህ ሠራተኞች እንዲቀጠሩ አቅጣጫ ሰጡ

የMIDROC Investment Group ሊቀመንበር ሼክ መሃመድ ሁሴን አል...

የወርቅ ማዕድን ሠራተኛው ከመገደላቸው በፊት ቤተሰባቸው ከታጣቂዎች ጋር ያደረገው የመጨረሻው የስልክ ምልልስ

ማስጠንቀቂያ፡ ቀጥሎ የሚያነብቡት ታሪክ ሊረብሽዎት ይችላል በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ...