በጠለምት ወረዳ በተከሰተ ድርቅ የ16 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለፀ

Date:

በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ መረው ቀበሌ በተከሰተው በረታች ድርቅ ሳቢያ የ16 ሰዎች ሕይወት ማለፉንና በመቶዎች የሚቆጠሩ የቤተሰብ አባላት ለስደት መዳረጋቸውን የመረው ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ ጥላሁን ገብረሚካኤል ተናግረዋል።

እንደ አስተዳዳሪው ገለጻ፣ በአካባቢው ከመጋቢት ወር ጀምሮ ምንም ዓይነት ዝናብ በመጥፋቱ አርሶ አደሩ የዘራው እህል ሳይበቅል ቀርቷል።

በዚህም ምክንያት በአካባቢው የምግብ እጥረትና ረሃብ በመከሰቱ፣ የሰው ሕይወት ከማለፉ ባሻገር የቁም እንስሳትም በሙሉ ማለቃቸውን አክለዋል፡፡

በተጨማሪም ድርቁ ያስከተለው የረሃብን ሁኔታ መቋቋም የተሳናቸው 488 አባወራዎች ከአካባቢው ለቅቀው ወደ ምዕራብ ትግራይ መሰደዳቸውን ጥላሁን አስረድተዋል።

ችግሩን በተመለከተ እስከ ክልል ድረስ አቤቱታ መቅረቡን የጠቆሙት አስተዳዳሪው፣ ከየቀበሌው የተመደቡ አካላት የሞቱ ሰዎችን፣ የተሰደዱ አባወራዎችን እና ያለቁ እንስሳትን ቁጥር መዝግበው ለሚመለከተው አካል ቢያሳውቁም እስካሁን ምንም ዓይነት ምላሽ አለመገኘቱን ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም ከመንግሥት የተደረገው ድጋፍ ለአቅመ ደካሞች ብቻ የተሰጠ የሴፍቲኔት እርዳታ እንደነበርም አክለው ጠቁመዋል።

እየከፋ የመጣውን የረሃብ አደጋ ተከትሎ የአካባቢው ነዋሪዎች የድንገተኛ እርዳታ ጥያቄ በማንሳት ሰልፍ መውጣታቸውን የገለጹት ጥላሁን፤ አሁንም አስቸኳይ ድጋፍ ካልቀረበ የአካባቢው ሕዝብ በረሃብ የሚያልቅበት አጋጣሚ ሰፊ በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት በፍጥነት እንዲደርሱላቸው ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

አዲስ ማለዳ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...