ከትግራይ ዩኒቨርሲቲ ታጣቂዎች ካልወጡ ተማሪ አንመድብም

Date:

ትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል የሚገኙ መቐለ፣ አክሱም፣ አዲግራት እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ግቢዎቻቸውን ከማንኛውም ወታደራዊ እንቅስቃሴ ነጻ እንዲያደርጉ ሰኞ ጷጉሜን 2 ቀን 2018 ዓ.ም. ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።

ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የፈረሙበትና ለአራቱ ዩኒቨርሲቲዎች የተጻፈው ደብዳቤ፣ በካምፓሶቹ ውስጥ የጦር ቁስለኞች እና ታጣቂዎች መቀመጣቸው መረጋገጡን ገልጾ፤ ይህ ሁኔታ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱን ከሲቪል ተልዕኳቸው ውጭ ለወታደራዊ ዓላማ በማዋል የተማሪዎችን ሕይወት ለአደጋ የሚያጋልጥ መሆኑን አሳስቧል።

በዚህም መሠረት ዩኒቨርሲቲዎቹ በግቢዎቻቸው የሚገኙትን ታጣቂዎች በአስቸኳይ እንዲያስወጡ እና ሀብቶቻቸው ለወታደራዊ አገልግሎት እንዳይውሉ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲያደርጉ ታዟል።

የዩኒቨርሲቲ ግቢዎች ከማንኛውም ወታደራዊ እንቅስቃሴ ነፃ መሆናቸው በአግባቡ ካልተረጋገጠ ተማሪዎችን እንደማይመድብ ያስታወቀው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ፣ ውሳኔው የተማሪዎች ደኅንነት እስኪረጋገጥ ድረስ ተፈጻሚ እንደሚሆን አስጠንቅቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 9 2019 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

-የግዮን እንግዳ አምዳችን :- ‹‹ምንጩና ጸሐፊው በማይታወቅ መረጃ መመራት አደገኛ...

ሸኽ መሃመድ አል አሙዲ ተጨማሪ 40 ሺህ ሠራተኞች እንዲቀጠሩ አቅጣጫ ሰጡ

የMIDROC Investment Group ሊቀመንበር ሼክ መሃመድ ሁሴን አል...

የወርቅ ማዕድን ሠራተኛው ከመገደላቸው በፊት ቤተሰባቸው ከታጣቂዎች ጋር ያደረገው የመጨረሻው የስልክ ምልልስ

ማስጠንቀቂያ፡ ቀጥሎ የሚያነብቡት ታሪክ ሊረብሽዎት ይችላል በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ...