ትምህርት እና ማህበራዊ ሚዲያ

Date:

ውድ ተማሪዎች፦

ዛሬ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ጥቂት ሰከንዶች የሚፈጅ ቪዲዮ በአንድ ሌሊት በብዙ ሰዎች ዘንድ ታዋቂ ሊያደርግ ይችላል። ይህም ብዙ ወጣቶች “ትምህርት ተምሬ ምን አገኛለሁ?” እንዲሉ እያደረገ ነው።

አንዳንድ * ታዋቂ * ነን የሚሉ ሰዎች ህይወት፣ ስኬት ያለው እዛ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ብቻ እንደሆነ በማሳየት የልጆችን አእምሮ፣ የወደፊት ተስፋና ህልም እየገደሉ ነው።

” TikTok ” ሆነ ሌላ የማህበራዊ ሚዲያ መጠቀም ወይም ይዘት መፍጠር በራሱ ችግር አይደለም፤ ችግሩ ግን የትምህርት፣ የንባብና የራስን እድገት ጊዜ ሲተካ ነው።

አስተውሉ ዝና ሊያልፍ ይችላል፤ እውቀትና ችሎታ ግን ማንም ሊነጥቃችሁ የማይችለው ሀብታችሁ ነው።

ትምህርት ምን ይሰጣል ?

ትምህርት መማር ፈተና ለማለፍ ብቻ አይደለም። ማሰብን ፣ መጠየቅን ፣ ችግር መፍታትን ፣ ትክክለኛውንና ስህተቱን መለየትን ፣ ሚዛናዊ መሆንን፣ ራስን መግዛትን ያስተምራል። የራስ እምነትን ያዳብራል፣ የሥራ እድልን ያሰፋል፣ አንድ ሰው የሚፈልገውን ህይወት ለመገንባት የሚያስፈልገውን እውቀትና ክህሎት ይሰጣል።

ዛሬ የምታሳልፉት ጊዜ ነገ የምትሆኑትን ሰው ይወስናል።

ሰዓታትን በስልክ ወይም በሌላ ስክሪን ላይ ብዙ ሰዓት ማሳለፍ ጊዜያዊ መዝናኛ ቢሰጣችሁም፣ በዚያ የምታጡት የጥናት ጊዜ ግን መልሳችሁ ልታገኙት አትችሉም።

📱 ተማሪዎች ማህበራዊ ሚዲያን ተጠንቀቁ ፤ ተጠቀሙበት እንጂ እሱ እንዳይጠቀምባችሁ!

TikTok ፣ Facebook ፣ Telegram፣ YouTube፣ Instagram፣ X እና ሌሎች የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ለመማር ፣ አዳዲስ እውቀቶችን ለማግኘትና ጠቃሚ ክህሎቶችን ለመማር ትልቅ እድል ይሰጣሉ። ነገር ግን ያለገደብ መጠቀም የጥናት ጊዜን ሊወስድ፣ ትኩረትን ሊበትንና የትምህርት ውጤትን ሊጎዳ ይችላል።

ስለዚህ ለማህበራዊ ሚዲያ የምታጠፉትን ጊዜ ወስኑ። በተለይ የጥናት ሰዓትን ለስልክ አትስጡ። ሌሊት ረጅም ሰዓት ስልክ መጠቀምም እንቅልፍን ስለሚያሳንስ በሚቀጥለው ቀን ትኩረታችሁን ሊጎዳ ይችላል።

የግል መረጃችሁን ጠብቁ።

የቤት አድራሻ፣ የስልክ ቁጥር፣ የትምህርት ቤት መረጃ፣ የቀጣይ መርሃ ግብር ወይም ሌሎች የግል መረጃዎችን ለማታውቋቸው ሰዎች አትስጡ። በኢንተርኔት ላይ የምትለቁት መረጃ በቀላሉ ሊሰራጭ እንደሚችል አትዘንጉ።

ወላጆች፣ የልጆቻችሁን የዲጂታል ህይወት ተከታተሉ።

ልጆች ስልክ እንዳይጠቀሙ ብቻ መከልከል ሳይሆን፣ ለምን ገደብ እንደሚያስፈልግ ከእነሱ ጋር ተወያዩ። እናተም አርአያ ሁናችሁ አሳዩዋቸው። ጊዜ ስጧቸው። ረጅም ሰዓት ቲክቶክ ወይም ሌላ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ባለማሳለፍ የምትመክሯቸውን እውነትም ኑራችሁ አሳዩዋቸው።

– የጥናት፣
– የእንቅልፍ፣
– የቤተሰብ ጊዜ
– የመዝናኛ ጊዜን በአግባቡ እንዲያመጣጥኑ እርዷቸው።

የጥናት ልምድ እንዲያዳብሩ፣ ጊዜያቸውን እንዲያቅዱ እና ለሚፈልጉት ሙያ ቀድመው እንዲዘጋጁ አበረታቷቸው።

የልጆቻችሁን የትምህርት ጉዞ በመከታተል ብቻ ሳይሆን፣ በመምራትና በመደገፍ አብራችሁ ተጓዙ።

ተማሪዎች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚያጠፉትን ሰዓት ወደ መጽሐፍ ንባብ፣ ትምህርት ነክ ይዘቶች፣ አዳዲስ ክህሎቶች፣ ስፖርትና ከቤተሰብ ጋር ወደ የሚያሳልፉት ጊዜ ማዞር ይችላሉ።

ውድ ተማሪዎች ፦ በአንድ ትንሽ ስህተት ፤ አልያም ከጊዜና ወቅት ጋር አብሮ የሚያልፈውን የማህበራዊ ሚዲያ ዝናን ሳይሆን ከእናንተ ጋር እስከመጨረሻው የሚቀረውን እውቀት ምረጡ ፤ እውቀት ያኮራል፤ ያስከብራል !

የ2019 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን ለተማሪዎች የእውቀትና የስኬት፣ ለወላጆች ደግሞ የደስታና የኩራት ዓመት እንዲሆን እንመኛለን።

መልካም የትምህርት ዘመን!

@tikvahethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 9 2019 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

-የግዮን እንግዳ አምዳችን :- ‹‹ምንጩና ጸሐፊው በማይታወቅ መረጃ መመራት አደገኛ...

ሸኽ መሃመድ አል አሙዲ ተጨማሪ 40 ሺህ ሠራተኞች እንዲቀጠሩ አቅጣጫ ሰጡ

የMIDROC Investment Group ሊቀመንበር ሼክ መሃመድ ሁሴን አል...

የወርቅ ማዕድን ሠራተኛው ከመገደላቸው በፊት ቤተሰባቸው ከታጣቂዎች ጋር ያደረገው የመጨረሻው የስልክ ምልልስ

ማስጠንቀቂያ፡ ቀጥሎ የሚያነብቡት ታሪክ ሊረብሽዎት ይችላል በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ...