በኒው ዮርክ በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ተገኝተው ሳለ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፤ የቴህራን ሰባት ነጥቦች ለዋሽንግተን ደርሰዋል። የዋይት ሀውስ ምላሽ በአሸማጋዮች በኩል እንደሚሰጣቸው እየጠበቁ ይገኛሉ።
“ዓላማችን አሜሪካ ቅድመ ሁኔታዎቻችንን እንድታውቅ ማድረግ ነው። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ኢራን ዕቅድ እንዳላትም ማወቅ አለበት። ቅድመ ሁኔታዎቹ ፍትሐዊ እና ምክንያታዊ ናቸው። አሜሪካ ሰላማዊ መፍትሔ እፈልጋለሁ ትላለች፤ እኛም ይሄንን መፍትሔ አቅርበናል” ብለዋል።
ኢራን በኒውክሌር መርሃ ግብሯ ላይ “መለሳለስ አሳይታለች” በሚል የወጡ ሪፖርቶችን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ውድቅ አድርገዋል።
“ባለፉት ሰዓታት ፕሮፓጋንዳዎች ሲሰሙ ነበር። የኢራን አቋም እንዳልተቀየረ ለመግለጽ እፈልጋለሁ። የሆርሙዝ ወሽመጥን የመክፈት ዕቅዳችንም ግልጽ ነው” ሲሉም አክለዋል።
