እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

Date:

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ ከፍተኛ ኃላፊነታቸው በቅርብ ወራት ውስጥ ለመልቀቅና ሕይወታቸውን ለክርስቶስ ለማዋል ያላቸውን ዕቅድ ይፋ አድርገዋል።

ጄነራል ሙሁዚ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልእክት፣ “የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው። እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ።

በጥቂት ወራት ውስጥ ይህንን ቢሮ ለብቁ ወታደራዊ መኮንን አስረክባለሁ፤ ከዚያም ሕይወቴን ለክርስቶስ እሰጣለሁ” ብለዋል።

ጄነራሉ ከኃላፊነታቸው መልቀቅ በኋላ ከሕዝብ እይታ ሙሉ በሙሉ እንደማይሰወሩ የገለጹ ሲሆን፣ በተጨማሪም በኡጋንዳ የመከላከያ ኃይል (UPDF) ውስጥ የሚያገለግሉ ወታደሮች ደመወዝ ወደ 2 ሚሊዮን የኡጋንዳ ሺሊንግ እንዲያድግ ጥሪ አቅርበዋል። የወታደሮች የመኖሪያ ሁኔታና ደመወዝ ማሻሻል ከቀጣይ ትኩረቶቻቸው መካከል መሆኑንም ጠቁመዋል።

ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ የኡጋንዳ ፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ልጅ ሲሆኑ፣ በመጋቢት 2024 የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ ሆነው ተሾሙ።

በወታደራዊ አመራርና በማኅበራዊ ሚዲያ የሚያስተላልፏቸው መልእክቶች በአፍሪካ ክልላዊ ፖለቲካ ውስጥ ተደጋጋሚ ትኩረት የሚስቡ ሰው ናቸው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...

የተጀመሩ የትምህርት ሪፎርሞችን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም በቁርጠኝነት መስራት ይገባል

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ...