ስምምነቱ የተፈረመው ዓድዋ ድል መታሰቢያ የተሳተፈበት እና ኅዳር 3 እና 4 ቀን “መጪውን መፍጠር” በሚል በሩሲያ ሞስኮ በተካሄደው 3ኛው ዓለም አቀፍ ሲምፖዚየም ላይ መሆኑን ተቋሙ ባጋራው መረጃ አስታውቋል።
ይህ አጋርነት የኢትዮጵያን የቅርስ ተቋማት ከዓለም አቀፍ ሙዚየሞች ጋር በማስተሳሰር፤ ለባለሙያዎች ልውውጥ፣ ለጋራ ምርምር፣ ለኤግዚቢሽን እና ለዘመናዊ የሙዚየም አስተዳደር ልምድ ቅብብል ትልቅ ዕድል ይፈጥራል ተብሏል።
የዓድዋ ድል መታሰቢያ ዋና ዳይሬክተር ዮሴፍ ቤኮ፤ በሁነቱ ላይ የተቋሙን ራዕይ እንዲሁም የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ እና የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሙዚየሞች የወደፊቱን ዕጣ ፈንታ በመቅረጽ ረገድ ያላቸውን ሚና በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።
