የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከሃንጋሪ የስፖርት ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ጋር የትብብር ስምምነት ፈረመ

Date:

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከሃንጋሪ የስፖርት ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ (HUSS) ጋር የሁለት ዓመት የትብብር ስምምነት (MOU) መፈራረሙ ተገለጸ።

በሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል መረጃ መሠረት፣ ስምምነቱ በሁለቱ ተቋማት መካከል የአካዳሚክ ትብብርን፣ የሙያ ልምድ ልውውጥንና የባህል ግንኙነትን ለማጠናከር ያለመ ነው።

ስምምነቱ እንዲፈጠር የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር አመንሲሳ ከበደ የጎላ ሚና እንደነበራቸው ምንጩ ገልጿል።

ዶክተር አመንሲሳ ከአንድ ወር በፊት በሃንጋሪ ቡዳፔስት በሚገኙ የስፖርትና የትምህርት ተቋማት በስፖርት ፊዚዮሎጂ ዘርፍ ባካሄዱት ምርምር ላይ በመመርኮዝ ሙያዊ ስልጠና እንደሰጡ ተጠቁሟል። በቆይታቸውም በመካከለኛና ከፍተኛ ከፍታ ባላቸው አካባቢዎች የሚሰጥ ስልጠና በአትሌቶች የአካል ብቃትና የውድድር ዝግጁነት ላይ ስለሚኖረው ተፅዕኖ ለስፖርት ፊዚዮሎጂ ተማሪዎች ማብራሪያና ስልጠና መስጠታቸው ተገልጿል።

በስምምነቱ ከተካተቱት ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል፦
• የመምህራንና የሠራተኞች ልውውጥ፤
• ለአትሌቶችና ለስፖርት ባለሙያዎች የሙያ እድገት የሚረዱ የትምህርት ዕድሎች፤
• በቅድመ ምረቃና በድህረ ምረቃ ደረጃ የተማሪዎች ልውውጥ፤
• የተግባር ልምምድና የጋራ ምርምር ፕሮጀክቶች፤
• ሴሚናሮችንና የባህል ልውውጥ መርሐ ግብሮችን ማካሄድ፤
• የአካዳሚክ ፕሮግራሞችንና ሥርዓተ ትምህርቶችን በጋራ ማዘጋጀትና ማሻሻል ይገኙበታል።

በሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል መረጃ መሠረት፣ ስምምነቱ አምስት አንቀጾችን የያዘ ሲሆን ለሁለት ዓመታት የሚቆይ ነው።

የትብብር ስምምነቱ እንዲመሠረትና ወደ ተግባር እንዲሸጋገር ዶክተር አመንሲሳ ከበደ ያበረከቱት አስተዋፅኦ በምንጩ ተጠቅሷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሞዛምቢክ አቻው ጋር ዛሬ ያደረገውን ወሳኝ ጨዋታ 1ለ0 ተሸነፈ !

በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ አራተኛ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ...

በአዲስ አበባ ለሶስት ቀናት የሚቆይ የንባብ ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው

የንባብ ባህልን ለማነቃቃት ያለመ 15ኛው ከተማ አቀፍ የንባብ ፌስቲቫል...

የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ የኤንሪኮ ማቴይ ሽልማት ተሸለሙ

የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በአፍሪካና በአውሮፓ መካከል ያለውን...