ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ፦ “እኔ የማላውቀው ፖለቲካ ነው”

Date:

ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ፣ በፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የተሰጣቸውን የአምባሳደርነት ሹመት በክብር እንደተቀበሉት ገለጹ።ፕሮፌሰሩ ሹመቱን በቀጥታ የሰሙት ከሚዲያ መሆኑን ለ“አዲስ ማለዳ” ጋዜጣ በሰጡት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል።

ሹመቱ ይፋ በተደረገበት ዕለት ስልካቸውን አጥፍተው በቦርድ አባልነት በሚያገለግሉበት የሳንቴ ሜዲካል ኮሌጅ የተማሪዎች ምርቃት ላይ እንደነበሩ ገልጸዋል። ከምርቃቱ በኋላ ስልካቸውን ሲከፍቱ የሹመቱን ዜና ከሚዲያ እንደሰሙ አስረድተዋል።

በመጀመሪያ ያገኟቸው መረጃዎች እውነተኛ ላይሆኑ እንደሚችሉ በመገመት ብዙም ትኩረት እንዳልሰጧቸው፣ በኋላ ግን መረጃው እየተጣራ ሲሄድ ሹመቱ እውነት መሆኑን እንዳረጋገጡ ተናግረዋል።

“አሁንም ቢሆን የት እንደምሄድ አላውቅም” ያሉት ፕሮፌሰር መስፍን፣ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በክብር እንደሚቀበሉ አረጋግጠዋል።

“ሌላም ቦታ መንግሥት ቢመድበኝ ለመሥራት ዝግጁ ነኝ። እኔ የማላውቀው ፖለቲካ ነው። ፖለቲካ ለማወቅ ብዙ እውቀትና ሥልጠና ያስፈልጋል” ሲሉም ተናግረዋል።

ከ1973 ዓ.ም. ጀምሮ ከ40 ዓመታት በላይ ለሕዝብና ለሀገር በማገልገል ላይ መሆናቸውን የገለጹት ፕሮፌሰር መስፍን፣ ለሀገር አገልግሎት አዲስ እንዳልሆኑ ጠቅሰዋል።

በሙያቸው ሐኪም መሆናቸውን በማንሳትም፣ በነፃነት መሥራት ምን እንደሆነ እንደሚያውቁና በዚህ ረገድ የሚያሳስባቸው ነገር እንደሌለ ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሞዛምቢክ አቻው ጋር ዛሬ ያደረገውን ወሳኝ ጨዋታ 1ለ0 ተሸነፈ !

በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ አራተኛ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ...

በአዲስ አበባ ለሶስት ቀናት የሚቆይ የንባብ ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው

የንባብ ባህልን ለማነቃቃት ያለመ 15ኛው ከተማ አቀፍ የንባብ ፌስቲቫል...

የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ የኤንሪኮ ማቴይ ሽልማት ተሸለሙ

የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በአፍሪካና በአውሮፓ መካከል ያለውን...