በአሜሪካ በበርካታ ባንኮች የኦንላይን አገልግሎት መቋረጥ ተከሰተ

Date:

በአሜሪካ በሚገኙ በርካታ ታላላቅ ባንኮች የኦንላይን አገልግሎት ላይ በተፈጠረ መስተጓጎል ምክንያት ሺዎች የሚቆጠሩ ደንበኞች የባንክ ሒሳባቸውን ማግኘትና የገንዘብ ዝውውር ማከናወን እንዳልቻሉ ተዘግቧል።

ችግሩ በመጀመሪያ በቼዝ ባንክ የተስተዋለ ሲሆን፣ በባንኩ ላይ የቀረቡ የቅሬታ ሪፖርቶች ቁጥር ከ10 ሺህ በላይ መድረሱ ተገልጿል። በተለይም ደንበኞች ወደ ባንኩ ድረ-ገጽ መግባትና የሒሳባቸውን ቀሪ ሂሳብ ማየት እንዳልቻሉ ቅሬታ አቅርበዋል።

በተመሳሳይ በባንክ ኦፍ አሜሪካ፣ ዩኤስ ባንክ እና ዌልስ ፋርጎ ደንበኞችም ተመሳሳይ የአገልግሎት መቋረጥ እንዳጋጠማቸው ሪፖርት ማድረጋቸው ተጠቁሟል።

በተጨማሪም የገንዘብ ማስተላለፊያ አገልግሎቱ ዜሌ ላይም መስተጓጎል መከሰቱ ተገልጿል። ከዚህ ጋር በተያያዘ የባንኮቹ አክሲዮኖች ዋጋ በገበያ ላይ በግምት ሁለት በመቶ መቀነሱ ተዘግቧል።

ለአገልግሎቱ መቋረጥ የዳረገው ትክክለኛ ምክንያት እስካሁን በይፋ እንዳልተገለጸ የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሞዛምቢክ አቻው ጋር ዛሬ ያደረገውን ወሳኝ ጨዋታ 1ለ0 ተሸነፈ !

በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ አራተኛ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ...

በአዲስ አበባ ለሶስት ቀናት የሚቆይ የንባብ ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው

የንባብ ባህልን ለማነቃቃት ያለመ 15ኛው ከተማ አቀፍ የንባብ ፌስቲቫል...

የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ የኤንሪኮ ማቴይ ሽልማት ተሸለሙ

የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በአፍሪካና በአውሮፓ መካከል ያለውን...