ክሪስታል ፓላስ ቶማስ ፍራንክን እንደ አዲስ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ

Date:

ክሪስታል ፓላስ የቀድሞውን የቶተንሃምና የብሬንትፎርድ አሰልጣኝ ቶማስ ፍራንክን አዲሱ ዋና አሰልጣኙ አድርጎ ሾሟል።

እስከ ሰኔ 2029 ድረስ የሚቆይ ውል የተፈራረመው ዴንማርካዊ በየካቲት ወር ከቶተንሃም ከተሰናበተ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አሰልጣኝነት ስራ ተመልሷል።

ፍራንክ በሰልኸርስት ፓርክ  ለስድስት ወራት ያህል ብቻ ቆይቶ ከስራ የተሰናበተውን ፈረንሳዊውን ፒየር ሳጅን ተክቶ ነው ስራውን ይጀምራል።

ፍራንክ ለክለቡ ይፋዊ ድረ-ገጽ በሰጠው አስተያየት፣ “እዚህ ተቀምጬ ይህን ድንቅ የእግር ኳስ ክለብ መምራት መቻሌ ትልቅ ክብር ነው፤” ብሏል። “ይህንን ኃላፊነት ለመወጣት በጉጉት እጠብቃለሁ።”

“ክሪስታል ፓላስ በእንግሊዝ እና በፕሪሚየር ሊጉ ውስጥ ትልቅ ስም ያለው ክለብ ነው። ተጫዋቾቹን እና በክለቡ ውስጥ ያሉትን ሁሉ ለመርዳት እና ለመደገፍ የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ፤ ከእነሱ ጋር ለመገናኘትም በጉጉት እጠብቃለሁ።”

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሞዛምቢክ አቻው ጋር ዛሬ ያደረገውን ወሳኝ ጨዋታ 1ለ0 ተሸነፈ !

በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ አራተኛ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ...

በአዲስ አበባ ለሶስት ቀናት የሚቆይ የንባብ ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው

የንባብ ባህልን ለማነቃቃት ያለመ 15ኛው ከተማ አቀፍ የንባብ ፌስቲቫል...

የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ የኤንሪኮ ማቴይ ሽልማት ተሸለሙ

የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በአፍሪካና በአውሮፓ መካከል ያለውን...