ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የልግስና ደረጃ 22ኛ ደረጃን ይዛለች

Date:

ኢትዮጵያ ዜጎቿ ከገቢያቸው በአማካይ 1.51 በመቶ ለበጎ አድራጎት በመለገስ፣ በ2026 የዓለም እጅግ ለጋስ ሀገራት ደረጃ 22ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧ ተገለጸ።

ወርልድ ፖፑሌሽን ሪቪው ባወጣው መረጃ መሠረት፣ ናይጄሪያ ከዓለም እጅግ ለጋስ ሀገራት ደረጃ ቀዳሚ ስትሆን ግብፅ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች።

ደረጃው የሀገራቱ ዜጎች ከግል ገቢያቸው ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ ለሃይማኖት ተቋማትና ለተቸገሩ ወገኖች የሚለግሱትን የገንዘብ መጠን በመቶኛ በማስላት የተዘጋጀ መሆኑ ተጠቅሷል።

ከዓለም ቀዳሚዎቹ 10 ለጋስ ሀገራት መካከል 6ቱ የአፍሪካ ሀገራት ሲሆኑ፣ ናይጄሪያ፣ ግብፅ፣ ጋና፣ ኬንያ፣ ዩጋንዳ እና ማላዊ ይገኙበታል። ቀሪዎቹ ቻይና፣ ህንድ፣ ኳታር እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ናቸው።

መረጃው በቀዳሚዎቹ 5 ደረጃዎች ውስጥ 4 የአፍሪካ ሀገራት መካተታቸውን በማመልከት፣ በአህጉሪቱ የመረዳዳትና የልግስና ባህል ጠንካራ መሆኑን ያሳያል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ  ህዳር  19 2019 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

-የግዮን ቆይታ  አምዳችን :- ‹‹ሰዎች ለምን የሕሊና ወንጀል እንደሚሠሩ አይገባኝም›› ኢንጂነር...

ራያ ከሲቲ ጨዋታ በፊት ወደ ሜዳ ሊመለስ ይችላል

የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ፣ ግብ ጠባቂው ዴቪድ ራያ ከማንቸስተር...

በኩዌት የድሮን ጥቃት ሁለት ጣሊያናውያን ተገደሉ

ጣሊያን በኩዌት ሁለት ዜጎቿን በገደለው የድሮን ጥቃት ኢራንን ተጠያቂ...

በየመን ከ700 በላይ ወታደራዊ ጥቃቶች ተፈጸሙ

የየመን መንግሥት ኃይሎች ባለፉት 24 ሰዓታት በሁቲ ታጣቂዎች ይዞታ...