በየመን ከ700 በላይ ወታደራዊ ጥቃቶች ተፈጸሙ

Date:

የየመን መንግሥት ኃይሎች ባለፉት 24 ሰዓታት በሁቲ ታጣቂዎች ይዞታ ላይ 726 ወታደራዊ ጥቃቶችን መፈጸማቸውን አስታወቁ።

በጥቃቶቹ 121 የሁቲ ታጣቂዎችና አዛዦች መገደላቸው ወይም መቁሰላቸውን የየመን ወታደራዊ ክፍል ቃል አቀባይ ኮሎኔል ማጄድ አል-ኑዛይሊ ገልጸዋል።

በመንግሥት ሥር ያለው የሳባ የዜና ወኪል እንደዘገበው፣ ጥቃቶቹ “የየመን ንጋት” በተሰኘው ዘመቻ ማዕቀፍ የተከናወኑ ሲሆን፣ 23 የአየር ጥቃቶች፣ 642 የመድፍ ጥቃቶች፣ 35 የድሮን ኦፕሬሽኖችና 26 የሮኬት ጥቃቶችን ያካተቱ ናቸው።

ጥቃቶቹ 81 ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችንና የተለያዩ መሣሪያዎችን ማውደማቸው ወይም መጉዳታቸውንም ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል።

የየመን መንግሥት ኃይሎች ዘመቻውን ያካሄዱት የሁቲዎችን ጥቃት ለመመከት፣ በይዞታዎቻቸውና በተጠባባቂ ኃይሎቻቸው ላይ ጫና ለማሳደር እንዲሁም ወታደራዊ አቅማቸውን ለማዳከም መሆኑን አስታውቀዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ  ህዳር  19 2019 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

-የግዮን ቆይታ  አምዳችን :- ‹‹ሰዎች ለምን የሕሊና ወንጀል እንደሚሠሩ አይገባኝም›› ኢንጂነር...

ራያ ከሲቲ ጨዋታ በፊት ወደ ሜዳ ሊመለስ ይችላል

የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ፣ ግብ ጠባቂው ዴቪድ ራያ ከማንቸስተር...

በኩዌት የድሮን ጥቃት ሁለት ጣሊያናውያን ተገደሉ

ጣሊያን በኩዌት ሁለት ዜጎቿን በገደለው የድሮን ጥቃት ኢራንን ተጠያቂ...

የነጋዴዎችን ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎች ተያዙ

በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የገቢዎች ቢሮ ሠራተኛ...