የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበርና ዋናው ስፖርት አጋር ሆኑ።

Date:

የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበርና ዋናው ስፖርት ትጥቅ አምራች ድርጅት የአጋርነት ስምምነት ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር እና ዋናው ስፖርት ትጥቅ አምራች ድርጅት በቀጣይ በጋራ ለመሥራት የአጋርነት ስምምነት ተፈራርመዋል።

በስምምነቱ መሠረት ዋናው ስፖርት ትጥቅ አምራች ድርጅት የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበሩ በቀጣይ ለሚያከናውናቸው ትልልቅ ፕሮጀክቶችና የተለያዩ እንቅስቃሴዎች የአጋርነት ድጋፍ እንደሚያደርግ የማህበሩ ፕሬዝዳንት ንዋይ ይመር ገልጸዋል።

ስምምነቱ የማህበሩን ጠቅላላ ጉባኤዎች ጨምሮ ሌሎች የማህበሩ ሥራዎችን ለማከናወን የድርጅቱ ድጋፍ የሚያካትት መሆኑንም ፕሬዝዳንቱ አስረድተዋል።

የዋናው ስፖርት ትጥቅ አምራች ድርጅት ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሀብተስላሴ ገብረክርስቶስ፣ ከማህበሩ ጋር በመተባበር መሥራታቸው ደስታ እንደሚሰጣቸው ገልጸው፣ ስምምነቱ የስፖርት ሚዲያው ለሀገር የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ከግምት ውስጥ በማስገባት የተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ስፖርቱን እንዲታወቅና እንዲወደድ የስፖርት ጋዜጠኞች የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው፣ ከማህበሩ ጋር በጋራ መሥራታቸው ኩራት እንደሚሰማቸው አቶ ሀብተስላሴ ገልጸዋል።

በቀጣይም የማህበሩን አቅም ለማጠናከርና የሀገሪቱን ስፖርት ወደ ተሻለ ከፍታ ለማድረስ በትብብር እንደሚሠሩ አቶ ሀብተስላሴ ገብረክርስቶስ አረጋግጠዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

መቻል አትሌቲክስ ክለብ ሶስት ዋንጫዎችን አሸነፈ

6ኛው የፔፕሲ አዲስ አበባ የክለቦች አቋም መለኪያ ውድድር በአዲስ...

በ7ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊጉ ሁለት ጨዋታዎች አቻ ተጠናቀቁ

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 7ኛ ሳምንት ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሀድያ ሆሳዕና...

በሰሜን ጎንደር በየወሩ ከ30 በላይ አዳዲስ የኤችአይቪ ተያዦች እየተመዘገቡ ነው

በሰሜን ጎንደር ዞን በየወሩ ከ30 በላይ አዳዲስ የኤችአይቪ ተያዦች...

12 ሀገራት የሚሳተፉበት የአፍሪካ መስማት የተሳናቸው እግር ኳስ ሻምፒዮና...