የቤቶች ኮርፖሬሽን የደንበኞች አገልግሎቱን ዲጂታል ሊያደርግ ነው

Date:

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የደንበኞችን አገልግሎት ቀልጣፋና ምቹ ለማድረግ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል ሥርዓት እንደሚቀይር አስታውቋል።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጫልቱ ሳኒ፣ የታቀዱ ሥራዎች በስኬት እንዲፈጸሙና የተጀመሩ ፕሮጀክቶች በፍጥነትና በጥራት እንዲጠናቀቁ ጠንካራ የክትትልና ግምገማ ሥርዓት መዘርጋት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

ኮርፖሬሽኑ በሩብ ዓመት የሥራ ግምገማው የተቋሙን ዕድገት ያስገኙ የለውጥ ሥራዎችን ማስቀጠልና አዳዲስ አሠራሮችን ተግባራዊ ማድረግ ላይ የተከናወኑ ተግባራትን መገምገሙን አስታውቋል።

የደንበኞችን ቅሬታ ለመቀነስ፣ የቤት አቅርቦትን በመጠንና በጥራት ለማሳደግ፣ የገቢ አማራጮችን ለማስፋትና ዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂዎችን ለመጠቀም በትኩረት እንደሚሠራም ጫልቱ ሳኒ ጠቁመዋል።

በተጨማሪም ፈጠራን የሚያበረታታ አሠራርን ተግባራዊ በማድረግና ተቋማዊ የማስፈጸም አቅምን በማጠናከር የተቋሙን አገልግሎትና የፕሮጀክቶች አፈጻጸም ለማሻሻል እንደሚሠራ ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ቀርጫንሼ ግሩፕና ጂሊ ሁለት ኤሌክትሪክ መኪናዎችን ለገበያ አቀረቡ

ቀርጫንሼ ግሩፕ ከቻይናው የመኪና አምራች ጂሊ ጋር በመተባበር ሁለት...

ማንችስተር ዩናይትድ 4-0 ተሸነፈ

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ብሬንትፎርድ ማንችስተር ዩናይትድን 4-0 በማሸነፍ ድል...

በሲዳማ የሕዝብ ማመላለሻ ላይ በደረሰዉ አደጋቨ 3 ሰዎች ሞቱ

በሲዳማ ክልል ከሀዋሳ ወደ በንሳ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ...

ከፈቃድ ውጭ የመማሪያ መጽሐፍትን ማተምና ለንግድ ማዋል ተከለከለ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር የመማሪያና ማስተማሪያ መጽሐፍት ዝግጅት፣ ሕትመት፣ ስርጭትና...