በየዓመቱ የሚካሄደው የአዲስ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል የመክፈቻ ፕሮግራም ዛሬ በጣልያን ካልቸር ኢንስቲቲዮት እደሚካሄድ ተገልጿል።
መክፈቻውም አምባሳደሮች፣የፊልም ባለሞያዎች፣የ ኢንሼቲቭ አፋሪካ ዋና ዳይሬክተር አቶ ክቡር ገና እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ይካሄዳል።
ለ አራት ቀን የሚካሄደው ፌስቲቫሉ ከግንቦት 13-ግንቦት 17 ድረስ በአራት የተለያዩ ማሳያ ቦታዎች ይካሄዳል።
የዘንድሮው ፌስቲቫል ለየት የሚያደርገው 28 የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑ ነው ሲሉ የ19ኛው አዲስ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል ኮርዲኔተር መና ሀይሌ ገልፀዋል።
አራቱ የማሳያ ቦታዎች የጣሊያን ካልቸር ኢንስቲቲዩት፣አሊያንስ ኢትዮ ፍራንሲስ፣ጎቲ ኢንስቲቲዩት እና የሀገር ፋቅር ቲያትር መሆናቸው ተገልጿል።
28ቱ ፊልሞች ከ 34 በላይ ሀገሮች የተሳተፉባቸው ሲሆን የተለያዩ የጣሊያን ፊልሞች እና ስድስት የኢትዮጵያ ፊልሞች ይገኙበታል።
የመክፈቻ እና የመዝጊያ ፕሮግራሙ በጣሊያን ካልቸር ኢንስቲቲዩት እንደሚካሄድ እና መግቢያ በ ነፃ መሆኑን የ 19ኛው አዲስ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል ኮርዲኔተር የሆኑት መና ሀይሌ ለ ግዮን መፅሄት ገልፀዋል።
