በአዲስ አበባ በተለያዩ የንግድ መደብሮች ላይ ለምግብ ማጣፈጫ ጥቅም ላይ የሚዉለዉ ኮረሪማ ዋጋው በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ብስራት ሬዲዮ ባደረገው ቅኝት ማወቅ ችሏል፡፡
ነዋሪዎች ለጣቢያችን እንደገለፁት በተለይም ካለፉት አስራ አምስት ቀናት ጀምሮ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ መኖሩን ተናግረዋል፡፡
በደቡብ ምእራብ ኢትዮጰያ ህዝቦች ክልል ከፋ ዞን በ17 ወረዳዎች የኮረሪማ ምርት በዋናነት የሚመረት ሲሆን በተጨማሪም በቤንች ሸኮ፣ በምዕራብ ኦሞ እና በሸካ ዞኖች በብዛት ይመረታል፡፡
ካፋ ዞን በብዛት የኮረሪማ ምርት የሚመርትበት ቢሆንም ከሰሞኑ በዞኑ ከ1ሺህ 500 መቶ እስከ 1ሺህ 700 እየተሸጠ መሆኑን እና ታይቶ የማይታወቅ ጭማሪ ማሳየቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
ኮረሪማ ከተተከለ ከ3 እስከ 5 ዓመት ቆይቶ ምርት መስጠት የሚጀምር ሲሆን አርሶ አደሮች ምርት መስጠት ከጀመረ በኋላ ከ7 እስከ 10 ዓመታት በየአመቱ ከ1 ሄክታር በአማካይ ከ30 ኩንታል በላይ ምርት ሊያገኙ እንደሚችሉ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡
በአዲስ አበባ በተለይም ካለፉት አስራ አምስት ቀናት ወዲህ የኮረሪማ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ዋጋው የጨመረበትን ምክንያት ብስራት ሬዲዮ የሚመለከታቸውን አካል አናግሮ በቀጣይ ምላሽ ይዞ ይመለሳል፡፡
