የአዲስ አበባ መታወቂያ የአገልግሎት ዘመን እና ሌሎች ማሻሻያዎች ሊደረጉለት  ነው

Date:

የከተማዋ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ እንዳስታወቀው በቀጣይ ወራት በስራ ላይ ያለውን  የነዋሪነት መታወቂያ ይዘት፣ የአገልግሎት ዘመን እና የገፅ ዲዛይን ከተማዋ ያለችበትን ደረጃ በሚመጥን እና ፋይዳን መሰረት ባደረገ እንዲሁም ሁሉን አቀፍ አገልግሎት የሚሰጥ /  Smart  Card/  አድርጎ ለማሻሻል ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝም አስታውቋል።

በተጨማሪም  ተቋሙ ለ 2 ሚሊዮን ነዋሪዎች የዲጂታል ካርድ መታወቂያን  መሰጠቱን ገልፆል።

ይህ የመታወቂያ የዲጂታል ምዝገባ የነዋሪን የባዮሜትሪክ መረጃን ያካተተ  እና ከ35 በላይ  ለማስረጃነት ጥቅም ላይ የሚውሉ የግለሰብ መረጃዎች  የሚመዘገቡበት ስርዓት መሆኑን ኢትዮ ኤፍኤም ከተቋሙ ያገኘው መረጃ  ይጠቁማል።

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የወረቀት መታወቂያ መስጠትን ለመጨረሻ ግዜ ማብቃቱን እና  ሙሉ ለሙሉ ወደ ዲጂታል ሽግግር መደረጉን  ባለፈው ሰኔ 25/2016ዓ.ም ይፋ ማድረጉን በመረጃው  አስታውሷል።

በተቋሙ የወሳኝ ኩነት ምዘገባን ጨምሮ በጠቅላላው ወደ 3 ሚልዮን የሚጠጉ ነዋሪዎች መረጃ በዲጂታል ምዘገባ የመረጃ ቋት ውስጥ እንዳለም አመላክቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ምግባረ-መልካሙ ኢትዮጵያዊ

ስለሺ መንገሻ - ከ1934 እስከ 2018 ዓ.ም ሠሎሞን ለማ ገመቹ. ግዮን...

ትራምፕ ለኔታንያሁ ማስጠንቀቂያ ሰጡ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ...

ኤምባሲዎችና የውጭ ባለሀብቶች በ«ፍራንኮ-ቫሉታ» ነዳጅ እንዲያስገቡ ተፈቀደ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ኤምባሲዎች፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና የውጭ...

የሪል ስቴት ኢንቨስትመንት ከዓመታዊ የትርፍ 90 በመቶውን እንዲያከፋፍሉ ሊደረግ ነው

የሪል ስቴት ኢንቨስትመንት ተብለው የሚቋቋሙ ፈንዶች ከዓመት ትርፋቸው ቢያንስ...