የአፍሪካ ቀንን በማስመልከት በአዲስ አበባ ከተማ የኪነ-ጥበብ ዝግጅት ተካሄደ

Date:

የአፍሪካ ቀንን ምክንያት በማድረግ ትናንት ማምሻውን በአዲስ አበባ አራት ኪሎ ፕላዛ ላይ በሰርከስ፣ በሙዚቃና በኪነ-ጥበብ በታጀበ መንገድ ተከበረ።

“የማካካሻ ፍትሕ ለአፍሪካውያንና ለትውልደ አፍሪካውያን” በሚል መሪ ሀሳብ የአፍሪካ ቀንን አስመልክቶ በተዘጋጀው የኪነጥበብ መርሐግብር ላይ  በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሂሩት ካሳው እንደገለፁት ፣ የአፍሪካ ቀንን በኪነ- ጥበብ ከማክበር ባሻገር የኪነ-ጥበብ ሚና ህብረተሰቡን በማስተማር፣ በማነቃቃት እና የጋራ እሴቶችን በማጠናከር ረገድ የላቀ መሆኑን ገልጸው በቀጣይ አዘጋጁ አካል እና አራቱ ማኀበራት በጥምረት በመሆን በከተማው የተለያዩ ክፍሎች መሠል መርሐግብሮች እንዲዘጋጁ የከተማው ባህል፣ ኪነ-ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ  ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ የሙዚቃ ዘርፎች ማኅበራት ህብረት ኘሬዝዳንት  ክቡር ዶክተር ዳዊት ይፍሩ በመድረኩ ላይ እንደገለፁት “አራቱ የሞያ ማኅበራት በጋራ በመሆን የአፍሪካ ቀንን በኪነ-ጥበብ ውስጥ በጋራ በመሰባሰብ ማክበር ትልቅ ትርጉም እንዳለው ገልጸው የኪነ-ጥበብ ዘርፎች መካከል ያለውን ትብብር ከማጠናከሩ ባሻገር፣ አፍሪካውያን በጋራ በመቆም የጋራ ችግሮቻቸውን መፍታት እንደሚገባ ተናግረዋል።

የሰላም ኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ሙልጌታ ለዝግጅት ክፍሉ በሰጡት ማብራሪያ “ሰላም ኢትዮጵያ ከኪነ-ጥበብ ማኅበራት ጋር በመተባበር ሰላምን፣ አንድነትን እና ማህበራዊ ለውጥን በኪነ-ጥበብ አማካኝነት ለማምጣት  በሚሰሩ ስራዎች ላይ ትኩረቱን አድርጎ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰርከስ ማህበር ጥምረት ፕሬዝዳንት አቶ ተክሉ አሻግሬ በበኩላቸው፣ የሰርከስ ጥበብ የባህል እና የማህበራዊ ትስስር ማዕከል በመሆን ህብረተሰቡን የማዝናናት፣ የማስተማር እና የማቀራረብ ሚና እንዳለው ገልፀዋል። የአፍሪካን ቀን በሰርከስ ጥበብ ማክበር የህዝቦችን ተሳትፎ ከፍ ከማድረጉም ባሻገር የባህል ልውውጥን እና የጋራ መግባባትን ያጠናክራል ብለዋል።

መርሐግብሩን ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ (ሲኤፍሲኤ) ፕሮጀክት አማካይነት ሠላም ኢትዮጵያ ፣ ከኢትዮጵያ የሙዚቃ ዘርፎች ማኅበራት ህብረት፣ ከኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር፣ ከኢትዮጵያ ሠዓሊያንና ቀራፅያን ማኅበር ፣ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰርከስ ማኅበር እንዲሁም ከአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብ እና ቱሪዝም በመተባበር በጥምረት አዘጋጅተውቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...