ሊቨርፑል ፣ አርሰናል፣ ማንችስተር ሲቲ፣ ቼልሲ፣ ኒውካስል እና ቶተንሃም በቀጣይ ዓመት በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ እንደሚሳተፉ ተረጋግጧል።
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዓመቱ የመጨረሻ ጨዋታዎች ዛሬ ሲደረጉ፤ አርሰናል ሳውዝሃምተንን 2 ለ 1 አሸንፏል። ለአርሰናል የማሸነፊያ ግቦቹን ኦዴጋርድ እና ቴርኒ አስቆጥረዋል።
በኦልድትራፎርድ ማንችስተር ዩናይትድ አስቶንቪላን 2 ለ 0 ሲያሸንፍ፤ አማድ ዲያሎ እና ክርስቲያን ኤሪክሰን የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ሊቨርፑል ከክሪስታል ፓላስ 1 ለ 1 ሲለያዩ ለሊቨርፑል መሀመድ ሳላህ፤ ለክሪስታል ፓላስ ደግሞ እስማኤል አሳር ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ቼልሲ ኖቲንግሃም ፎረስትን 1 ለ 0 ሲያሸነፍ ኒውካስትል በኤቨርተን1 ለ 0 ተሸንፏል።
በሌሎች ጨዋታዎች በርንማውዝ ሌስተር ሲቲን 2 ለ 0፤ ማንችስተር ሲቲ ፉልሃምን 2 ለ ዐ፤ ቶተንሃም በብራይተን 4 ለ 1 ሲያሸነፉ ብሬንትፎርድ ከ ወልቭስ 1 ለ 1 አቻ ተለያይተዋል።
