የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን ጨምሮ የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት
ወይዘሮ ሳራ ሀሰን፣ኢንስትራክተር አድማሱ ሳጂ፣
አቶ ቢኒያም ምሩፅ እና የፌዴሬሽኑ ምክትል ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ማስተዋል ዋለልኝ ዛሬ በታላቅ ድምቀት ለሚጀመረው 13ኛው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች እና 4ኛው ከ18 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ለመታደም ድሬዳዋ ገብተዋል ።
በድሬዳዋ ዓለምአቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ካሊድ መሀመድ ፣የድሬዳዋ አስተዳደር አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ዮናስ በትሩ እና ሌሎች አመራሮች ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል ።
በተጨማሪም በከተማዋ የተሰሩ የኮሪደር ልማት እና ሻምፒዮናው የሚካሄድበት ድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ጎብኝተዋል።
ሻምፒዮናው ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሰባት ቀናት ይካሄዳል ።
