መስከረምን_ዐየኋት!

Date:

ስለ መሥከረም አበራ ከዚህ ቀደም ከማን ከማን ጋር አውርቻለሁ? . . . ቴዲ ተ/አረጋይ፣ እንዳለ ጌታ ከበደ፣ ዳግማዊ ፈይሳ፣ ዶ/ር ተሻለ አሰፋ . . . በተለያዩ ምክንያቶች ስለሷ አንስተውልኛል፡፡ ዛሬ ደግሞ መሥከረም ጥሩ ተዋናይ መሆኗን የሚመሰክር ብቻ ሳይሆን “ሰው” መሆን የምትችል መሆኗን የሚያስረዳ ግሩም ቆይታ የዳዊት ተስፋዬ “ደጃፍ” ላይ በተመስጦ ተመለከትኩ፡፡

“ለምን ጥሩ ተዋናይ . . . “ሰው” መሆኗን” አልኩኝ?

ለእኔ ጥሩ ተዋናይ “መድረክ ላይ ሲወጣ ራሱን ይዞ የማይወጣ፣ ከመድረክ ሲወርድ መድረኩን ይዞ የማይወርድ” ነው፡፡ የመሥከረም የደጃፍ ላይ ቃለ ምልልስ (ጨዋታ ልበለው መሰል) ይኼንን በሚገባ ያሟላል፡፡ መሥከረም የመድረኩና የሲኒማው ገጸባህርያት ተከትለዋት ስቱዲዮ አልገቡም፡፡ ንጹህ ወጓ፣ ሳቋቋ፣ ድምጿ፣ አካላዊ እቅስቃሴዋ፣ የፊት ገጽታዋ፣ ግልጽ ንግግሯ . . . ከመድረክ ያልተቀዳ ከስክሪን ያልተዛመደ ገራገር፣ ተወዳጅ፣ ወትሯዊ ሆኖ ተሰምቶኛል፡፡

“ሰው”ነቷ፡- በሕይወቷ መንገድ ሁሉ ላይ ለሚያጋጥሟት ስኬቶች በር ከፈቱላትን የሚታወቁና የማይታወቁ ግለሰቦችን በሚገባ ዕውቅና የሰጠችበት ማስተዋሏ ማርኮኟል፡፡ ዕብሪት በሌለው መንገድ ለሥራዋ ስኬት አስተዋዖ የነበራቸውን ባለሙያዎች በልካቸው በትህትና እና በቀናነት በነርሱ ትከሻ ላይ ቆማ እንደታየች ስትመሰክር የሷን ሰማይን ለመንካት መንጠራራት ኢምንት ታደርጋቸዋለች፡፡ የመውደዷን ልክ የምትገልጽበት መንገድ የህጻን ልጅ ፍቅር ያኽል ያሳሳል፡፡ እመቤት፣ ፍቃዱ፣ ጌትነት፣ ጫኔ፣ ዳግማዊ፣ አብርሃም፣ ዋጄ፣ ሙሉዓለም፣ ጀማነሽ፣ ተሸለ . . . እልፍ ስሞች በቁልምጫ ሲጠሩ ልባዊ ስሜቶቿ ይደመጣሉ፡፡

የማታውቀውን ካለማስመሰል “አላውቀውም” ማለቷ፣ ለሙያዎች ያላት አክብሮት ከትህትና ገዝፎብኛል፣ ለቴአትር፣ ሲኒማ፣ ሙዚቃ፣ ግጥም. . . ያላት መወዳጀት፣ በዕብሪት አለመታፈኑ ነገዋ ያማረ እንደሆነ ያመላክታል፡፡ የመሥከረምን ጥቂት የቴሌቪዥን ቃለ መጠይቆች ከዚህ ቀደም ሳላይ አልቀረሁም፡፡ የዳዊት ተስፋዬን ያኽል ግን መሥከረምን ያስተዋወቀን ያለ አይመሥለኝም፡፡ ደጃፍ የምር “በላ አይይኽ” የሚሉት ምርጥ ፖድ ካስት መሆኑን ለማያውቁት ብቻ የምመሰክረው እውነት ነው፡፡

ከይታገሱ ጌትነት

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...