የሩሲያ ቋንቋ ወደ ኢትዮጵያ የገባው በፍቅር ነው

Date:

በፈረንጆቹ ሰኔ 6 ቀን 2025 ዓ.ም  የሚከበረውን የሩሲያ ቋንቋ ቀን በማስመልከት ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ቆይታ የነበራቸው ደራሲና ጸሃፌ-ተውኔት  አያልነህ ሙላቱ፣ የሩሲያ ቋንቋ ወደ ኢትዮጵያ የገባው በትምህርት ስርዓት ውስጥ እንደ አንድ የውጭ ቋንቋ ስለተዋቀረ ሳይሆን በራሱ ፈቃድና ኃይል ነው ብለዋል።

“የሩሲያ ቋንቋ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ ተራማጅ የሆነ አመለካከት ይዞ ነው የገባው፡፡ በሩሲያ ቋንቋ ስትማር የምታገኘው ፑሽኪንን ነው፣ ዶስተዬቭስኪን ነው፣ ቼሃቭን ነው፣ ቶልስቶይን ነው። ይህንን ሥነ-ጽሑፍ በራሱ ቋንቋ ማንበብ ምን ያህል ጠቀሜታ እንዳለው ጉጉት ስለሚያሳድርብህ፣ የአንባቢያን ወይም የቋንቋው ተማሪዎች ከእለት ወደ ዕለት መጨመሩ አንዱ ምክንያት  ይሄ ይመስለኛል” ሲሉ በኢትዮጵያ ስላለው የሩሲያ ቋንቋ ፍላጎት ገልጸዋል።

አክለውም፤ ሩሲያኛን መማር የነጻ ትምህርት እድል ሊያስገኝ መቻሉ አንዱ ትልቁ የስህበት ምክንያት እንደሆነ ተናግረዋል።

“በሦስተኛ ደረጃ ሩሲያ ከኢትዮጵያ ጋር ለረጅም ዘመን ትልቅ የሆነ የወዳጅነት ግንኙነት ያላት፤ በእምነትም በተለያዩ ጉዳዮችም ከኢትዮጵያ ጋር ምንም ዓይነት ተቃርኖ የሌላት፤ በታሪክ ሩሲያ የቅኝ ግዛት ስርዓትን ተከትላ መሳሪያዋን ያላነሳች እንዲያውም ቅኝ ገዢዎችን የምትፋለም፣ ለነጻነት የቆመች ሀገር መሆኗን ኢትዮጵያውያን፣ ወጣቱም ያውቃል፡፡ እና ይሄም ራሱ  የሩሲያ ቋንቋን ለመማርና  ሩሲያን ለማወቅ የገፋፋ ይመስለኛል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...