የኢትዮጵያ ዋንጫ የ2017 ዓ/ም የውድድር ዘመን ፍፃሜ በወላይታ ዲቻ እና ሲዳማ ቡና መካከል ዛሬ እሁድ ሰኔ 1 ከቀኑ 9:00 ሠዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚከናወን መገለጹ ይታወቃል።
ነገር ግን ጨዋታው በዝግ እንዲካሄድ የተወሰነ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ገልጾ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ETV) እና በሌሎች ቻናሎች በቀጥታ የሚተላለፍ ሲሆን ደጋፊዎች ይህንኑ አውቀው ጨዋታው በሚተላለፉባቸው ቻናሎች እንዲከታተል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።
