“የፅጥታዉ አካል የፅጥታ ስጋት አለብኝ ካለ እሱን የመቀበል ግዴታ አለብን”

Date:

 
የኢትዮጲያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ባህሩ ጥላሁን:

የኢትዮጲያ ዋንጫ የፍፃሜ ዛሬ በሲዳማ ቡና እና በወላይታ ድቻ መካከል በአድስ አበባ ስታዲየም የሚደረግ ሲሆን ትናንት ማምሻዉን ፌዴሬሽኑ በማህበራዊ ሚዲያ ገፁ ላይ ከአቅሜ በላይ በሆነ ምክንያት ደጋፊዎች ወደ ሜዳ አይገቡም ሲል አሳዉቋል።

ይህም በርከት ያሉ ደጋፊዎች በረካታ ኪሎሜትሮችን አቋርጠዉ ወደ አድስ አበባ ከመጡ በኅላ ይህ ዉሳኔ መወሰኑ ብዙዎችን አስቆጥቷል።

በጉዳዩ ዙሪያ ለብስራት ቴሌቪዥን ስፖርት ዝግጅት ክፍል ጋር ቆይታ ያጀረጉት የፌዴሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ባህሩ ጥላሁን “በእኛ በኩል የዝግጅት ችግር የለም ከፀጥታዉ አካል የፀጥታ ችግር አለብኝ ካለ እሱን የመቀበል ግዴታ አለብን ብለዋል”።

አቶ ብሀሩ አያይዘዉም “ፖሊስ የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት የሚሆኑ ምልክቶችን አይቻለሁ መረጃ ደረሶኛል ካለ ምንም ማድረግ አንችልም እግርኳሱም እሚኖረዉ ሀገረ ሰላም ስትሆን ነዉ።ይህን ደግሞ አለመቀበል አንችልም ሲሉ ገልፀዋል”።

ዉሳኘኔዉን በምሽት ማሳወቃችን ወይም ደግሞ ቀድመን ያላሳወቅንበት ምክንያት የኛ ችግር ሳይሆን እንደፌዴሬሽን ዝግጅታችን አጠናቀን ጨዋታዉን በመጠባበቅ ላይ እያለን ይህ ዉሳኔ በዛ ስዓት ደርሶናል የደረሰንን ዉሳኔ ደግሞ በስዓቱ አሳዉቀናል ሲሉ ስራ አስፈፃሚዉ ተናግረዋል።

የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ቀን 9 ስዓት ላይ በአድስ አበባ ስታዲየም በዝግ የሚደረግ ሲሆን ጨዋታዉ በኢቲቪ የቀጥታ ሽፋኝ ይሰጠዋል ተብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...

ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት እውቅና ሰጠ

የፖርቹጋሉ ክለብ ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት ማሪያ ዶሎሬስ...

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...