ሲዳማ ቡና ወላይታ ድቻን 2ለ1 በሆነ በማሸነፍ የኢትዮጵያ ዋንጫ ሻምፒዮን መሆን ችለዋል።
የሲዳማ ቡናን የማሸነፊያ ግብ መስፍን ታፈሰ እና ሀብታሙ ታደሰ ከመረብ ሲያሳርፉ ለወላይታ ድቻ ካርሎስ ዳምጠው አስቆጥሯል።
ሲዳማ ቡና በሚቀጥለው አመት ኢትዮጵያን በመወከል በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውድድር የሚሳተፉ ይሆናል።
ወላይታ ድቻ ባለፉት ተከታታይ ሁለት አመታት የኢትዮጵያ ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ ተሸንፈዋል።
