የአንድነት ኢትዮጵያ የቤት ሰራተኞች ማህበር የህብረቱ ፕረዝደንት ሒሩት አበራ ስምምነቱ ኢትዮጵያ ከፈረመች አመታት ቢቆጠሩም እስካሁን ተግባራዊ አልሆነም ብለዋል።
ፕሬዚዳንቷ የቤት ሰራተቾች በማህበረ ተደራጅተው ስለመብቶቻቸው ያለመጠየቅ፣እንደ ማኒኛውም ሰራተኛ የሰራተኞችን መብት በሚያስጠብቀው በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ 1156 ውስጥ እንዲሁም በሌልች የህግ ማእቀፍ ውስጥ ያለመካተታቸውና ያለመጠየቃቸው እስካሁን አዋጁ ሳይፀድቅ ቆይቷል ብለዋል።
ስለቤት ውስጥ ሰራተኞች የሚያወሳውን አለም አቀፍ ስምምነት 189 ኮንቬንሺን ለምን አልተፈረመም ብለን ስንጠይቅም ከሀገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ጋር የማይጣጣም ነው ይባላል በህግ አውጪው በኩል ሲሉም አስረድተዋል።
መመሪያው ፀድቆ በስራ ላይ ቢውል፣ የቤት ሰራተኞችን መሰረታዊ መብቶች የሚያስጠብቅ፣ ከአሰሪዎቻቸው ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነት የሚያስተካክልና የስራ ከባቢያቸውንም ምቹ እንዲሆን የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡
ከሁሉም በላይ ግን፣ መመሪያውና የስራ ቅጥር ውሉ፣ የቤት ሰራተኞች ጉልበታቸው ሲደክም እንደ ጡረታ ያሉ የማህበራዊ ዋስትና አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያደርግ ነው በማለት ገልፀዋል፡፡
በአሁን ወቅት የቤት ሰራተኞች በስራና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የሚዋዋሉት ውል ምንም ዓይነት ህጋዊ መሰረት የሌለው፣ ሐላፊነትን የማይሰጥና መብትና ግዴታን የማይለይ ነው፡፡
ሆኖም ይህን ችግር ለመፍታት ነው ማህበሩ የተቋቋመው ያሉ ወ/ሮ ህሩት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራን እንገኛለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ከአራት አመታት በፊት በተደረገ የዳሰሳ ጥናት መሰረት፣ በሀገሪቱ ወደ 5 ነጥብ 6 ሚሊዮን የሚገመቱ ሰራተኞች እንዳሉ የገለፁት ፕሬዚዳንቷ፣ እነዚህ ዜጎች የተለያዩ ችግሮች እንደሚደርሱባቸውም በጥናት አረጋግጠናል ብለዋል፡፡
