የእስላማዊት ኢራን አብዮታዊ ዘብ( IRGC) ዋና አዛዥ በእስራኤል ጥቃት ተገደሉ፡፡
አብዮታዊ ዘቡ ሁሴን ሳላሚ ቢገደሉበትም አጸፋዊ ምላሽ በአፋጣኝ ለእስራኤል ጥቃት እንደሚሰጥ አስጠንቅቋል።
ሳላሚ አገራቸውን በመጠበቅ ላይ ሳሉ ሰማዕት ሆነዋል ያለው ዘቡ አሜሪካም አብራ ከባዱን ዋጋ ትከፍላለች ሲል ዝቷል።
ለጠላት “ጽዮናውያን ምላሹ” በእጃችን ነው ያለው ጦሩ ከባድ ውደመት እስራኤል መፈጸሟን አልደበቀም።
እስካሁን በተረጋገጠው ዜና መሰረት እስራኤል አምስት ዙር የጥቃት ማዕበል በኢራን ላይ መፈፀሟን አልጀዚራ አስነብቧል።
