የ USAID ድጋፍ በመቋረጡ መንግስት ከራሱ ካዝና ከፍተኛ በጀት መደበ

Date:

ባለፈው ጥር ወር ወደ ስልጣን የመጡት ዶናልድ ትራምፕ ከወሰዷቸው አበይት ውሰኔዎች መካከል የ  USAIDን ስራ መዝጋት ነው በዚህም በርካታ አገራት ያገኙ የነበረው ድጋፍ እንዲቋረጥ ሆኗል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ የ2018 በጀቱን ለፓርላማ ያቀረበው መንግስት ለጤናው ዘርፍ ከራሱ ካዝና የመደበው በጀት እንዲጨምር አስገድዶታል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ በበጀት ንግግራቸው ወቅት ይሄን አረጋግጠዋል።

ስም ባይጠሩም አንዳንድ አገራት ድጋፍ በማቋረጣቸው መንግስት ለጤናው ዘርፍ በተለይ ለመድሃኒት ግዥ ከራሱ ከፍተኛ በጀት ለመያዝ ተገዷል ብለዋል።

በርግጥ አገራቱ ድጋፉን መልሰው እንደሚጀምሩ እየገለፁልን ነው ሲሉ አክለዋል።

ለ2018 በጀት አመት መንግስት ለጤና ዘርፍ በካፒታል ወጪ ከራሱ ቋት 32 ቢሊየን ብር መድቧል።

በተጨማሪ በእርዳታ 16 ቢሊየን እንደሚገኝ ነው የገለፀው።

ይህ ሁኔታ የ2017 በጀት ቀመር ላይ የተለየ ነበር።  በ2017 በጀት አመት ለጤና ዘርፍ ተይዞ ከነበረው የካፒታል ወጪ እርዳታ 12 ነጥብ 6 ቢሊየን ከመንግስት ካዝና አራት ቢሊየን ብር ነበር።

ቅዳሜ ገበያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...