“ሞቢሊቲ ኢ”  50 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለደንበኞች አስረከበ

Date:

“ሞቢሊቲ ኢ” የተሰኘው ድርጅት በእህት ኩባንያው “ድጋፍ ማይክሮ ፋይናንስ” ቆጥበው ሲጠባበቁ ለነበሩና ለብድር ብቁ ለሆኑ ደንበኞቹ በአምስተኛ ዙር 50 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በዛሬው ዕለት አስረክቧል።

ለደንበኞች ተሽከርካሪዎቹ 50 በመቶ ቅድመ ክፍያ በመፈፀም ፤ቀሪውን ከድጋፍ ማይክሮ ፋይናንስ በሚመቻች ብድር በ16 ነጥብ 5 በመቶ ወለድ እንደሚቀርብ ተገልጿል።

በዚህም መሠረት በድጋፍ ማይክሮ ፋይናንስ ቆጥበው ሲጠባበቁ የነበሩና ለብድር ብቁ የሆኑ 50 ደንበኞች የአምስተኛ ዙር የቢ ዋይ ዲ መኪኖችን ተረክበዋል።

በቀጣይም “ሞቢሊቲ ኢ” የተለያዩ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ለደንበኞች ለማቅረብ ዝግጅት ማድረጉን የሲኖ አፍሪካ ትሬዲንግ ዋና ሥራ አስኪያጅ አ/ቶ ሚሊዮን ጌታቸው ተናግረዋል።

“ሞቢሊቲ ኢ” በ4 ዓመት የብድር ክፍያ መመለሻ ጊዜ ያቀረበውን ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ልዩ ቅናሽ ሪፌንቲ በሚገኘው ዋና ማሳያው እንዲሁም መስቀል ፍላወር እና ሃዋሳ ፒያሳ ሩት ገበያ በሚገኙት ቅርንጫፎች አመቻችቶ ተጨማሪ ዙር መኪኖችን ለማስረከብ ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ገልጸዋል።

“ሞቢሊቲ ኢ” ከዚህ ቀደም በአራት ዙር
ከቢዋይዲ ሲጉል፣ ቢዋይዲ ኢ 2፣ ቢዋይዲ ዩአን አፕ፣ ቢዋይዲ ዩአን ፕላስ እና ቢዋይዲ ሶንግ ፕላስ ተሽከርካሪዎችን በ50 በመቶ ቅድመ ክፍያ ቀሪውን ከድጋፍ ማይክሮ ፋይናንስ ጋር በመተባበር ማቅረቡ ይታወሳል።

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...