አያቶላ ኻሚኒ አሜሪካ ኢራንን ብታጠቃ ከባድ ጉዳት እንደሚያጋጥማት አስጠነቀቁ

Date:

የኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አያቶላ አሊ ኻሚኒ ዩናይትድ ስቴትስ ኢራንን ብታጠቃ ከባድ መዘዝ የሚያመጣ ዘላቂ ጉዳት እንደሚያጋጥማት  አስጠነቀቁ።

የአሜሪካ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ትናንት ለኢራን መሪዎች በተለይም ለአያቶላ ኻሚኒ ኢራን ያላንዳች ቅድመ ሁኔታ እጅ መስጠት አለባት የሚል መልዕክት ማስተላለፋቸው ይታወሳል።

ይህንንም ተከትሎ የኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አያቶላ አሊ ኻሚኒ፣ የኢራንን ህዝብና ታሪኳን የሚያውቁ አስተዋዮች ኢራንን በዚህ መልኩ ዛቻ በተሞላበት ቃላት  አይናገሯትም  ብለዋል፡፡

ምክንያቱም ኢራናውያን ለጠላት የሚንበረከኩ ህዝቦች አይደሉም ሲሉ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

መንፈሳዊ መሪው  አያይዘውም፤ ዩናይትድ ስቴትስ ከእስራኤል ወግና ኢራንን ማጥቃት ከጀመረች  ከባድ እና ዘላቂ ጉዳት እንደሚደርስባት አስጠንቅቀዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...