የአትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ያሰለጠናቸውን የፖሊስ መኮንኖች አስመረቀ

Date:

የአትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ በማስተርስ፣ በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በድህረ ምረቃ ዲፕሎማ እና በመደበኛ ሠርተፊኬት በተለያዩ  የትምህርት መርሃ-ግብር ያሰለጠናቸውን ስትራቴጂክና መካከለኛ የፖሊስ መኮንኖች በዛሬው ዕለት በታላቅ ድምቀት አስመርቋል።

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ስላሴ ለተመራቂዎቹ ባስተላለፉት መልእክት፣  ሀገራችሁን በቀናነት በታማኝነትና በልበ በሙሉነት ለማገልገል በተዘጋጃችሁበት እንዲሁም ነገን በተስፋ ብርሃን የሚታዩበት ጸዳል በመሆኑ ልትኮሩና ትልቅ ቦታ ሊትሰጡት ይገባል ብለዋል።

አክለውም፤ የህግ የበላይነትን ማስከበር ወንጀል መከላከልና የሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን ማስጠበቅ የመንግስት የቁልፍ ተግባር ቢሆንም ሰላም የሰው ልጆች ሁሉ ቀዳሚና የማይተካ በረከትና ጸጋ በመሆኑ የመላው ህዝባችንን ትጉ ተሳትፎና ትብብርን  እንደሚጠይቅ ተናግረዋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በከፍተኛ እድገት ውስጥ ያለች፣ ብዙ ታላላቅ ድሎችን እያሳካች ነው ያሉት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል፣ በቀጣይም በውስጥና በውጭ ሆነው ሀገራችን ላይ አደጋ ለማድረስ የሚቃጡ  ጠላቶችን መመከት የሚያስችል ጠንካራ የፖሊስ ኃይል እንደ ሀገር መፈጠሩን ጠቁመዋል።

በሪፎርሙ ዘመኑን የዋጀ የማድረግ አቅሙ ያደገ የፖሊስ ተቋም መፍጠር ተችሏል ያሉት ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል፣ ማንኛውንም ግዳጅ የአካልም ሆነ የህይወትም መስዋዕትነት ከፍሎ የህዝብ ደህንነት መጠበቅ የሚችል የፖሊስ ኃይል መፍጠር ችለናል ብለዋል። እንደ ትላንቱ ሁሉ የሀገራችን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ በፅናት እንቆማለን በማለት የሠራዊቱን ቁርጠኝነት ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን አበበ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲም የሀገራችንን የፖሊስ የሙያ ዘርፍ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የፖሊስ ትምህርት እና ስልጠና ጥራት በማሻሻል ፣ ብቁ እና ፕሮፌሽናል የፖሊስ ሰራዊት በማፍራት ላይ ይገኛል ነው ያሉት። 

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በአሁኑ ሰዓት ዘመኑ ያፈራቸውን ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም ህዝብ እና መንግስት የጣለበትን ህገ-መንግሱቱንና ሌሎች የሃገሪቱን ህጎች የማክበር፣ የዜጎችን መብትና ጥቅም እንዲሁም ሠላምና ደህንነትን ከማናቸውም ጥቃቶች የመከላከልና ጠበቅ ኃላፊነቱን በብቃት እየተወጠ ብለዋል ፕሬዝዳንቱ። መረጃው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ኢትዮጵያ እስከ 2028 ዓ.ም. ድረስ 4 ሚሊዮን ገበሬዎችን በዲጂታል ለመመዝገብ አቅዳለች

ኢትዮጵያ እስከ 2028 ዓ.ም. ድረስ አራት ሚሊዮን ገበሬዎችን በአገር...

ሕገ-ወጥና ጊዜያቸው ያለፈ ምርቶችን ሲሸጡ በተገኙ 52 ተቋማት ላይ እርምጃ ተወሰደ

የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን የሕብረተሰቡን ጤናና ደኅንነት ለመጠበቅ...

ከጥር 1 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ ለጫት ላኪዎች የቅድመ ፈቃድ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት መስጠት ይቆማል

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከጫት ወጪ ንግድ ፈቃድና የብቃት...

ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ሠራተኞች ይፈለጋሉ

በኢትዮጵያ ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ክፍት የመንግሥት የሥራ መደቦች መኖራቸውንና...