“ቆፍጠን ያለ ውይይት ከፑቲን ጋር” ኢራን

Date:

የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ከፑቲን ጋር ሊማከሩ ወደ ሩሲያ ሊያቀኑ ነው፡፡

ውስብስብ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ለመመካከር ወደ ሞስኮ የሚያቀኑት የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሜሪካ ከዓለም አቀፉ ህግ ውጭ ሆናለች ብለዋል።

ሰኞ በክሬምሊን ስለቁልፍ ጉዳዮች ከፑቲን ጋር እንነጋገራለን በሚል መግለጫ ሰጥተዋል አባስ አራግቺ።

“ሩሲያ የኢራን ወዳጅ ናት እናም ስትራቴጂክ ጥምረታችንን በአግባብ እየተጠቀምንበት ነው”በሚል በኢስታንቡል ቱርክ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰተዋል ሰይድ አባስ አራግቺ፡፡

ሁል ጊዜም እንመካከራለን አቋማችንንም እናስተባብራለን ነው ያሉት አራግቺ፡፡

ከፑቲን ጋር ቆፍጠን ያለ ምክክር ይኖረናል እናም አንድ ላይ ሆነን መስራታችንንም እንቀጥልበታለን በሚል ብርቱ መግለጫ አውጥተዋል፡፡

ቴህራን ከሞስኮ ጋር በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ እንደምትሰራ ያረጋገጡት አባስ አራግቺ ዲፕሎማሲውን መሰናክል የሆነችበት አሜሪካ እንጂ እኛ አይደለንም በሚል ወቅሰዋል።

ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ የቻይናው ሺ ጂንፒንግም ሆነ የሩሲያው ፑቲን ድምጽ በአሜሪካ ጥቃት ዙሪያ  አልተሰማም።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ካናዳ ምዝገባም ሆነ ስምሪት አልተጀመረም

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መቀመጫውን ካናዳ ካደረገው "ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል"...

የክቡር ዶክተር ጋሽ መሐሙድ አዲስ አልበም ለአድማጮች ሊደርስ ነዉ

ታዋቂው ድምፃዊ ክቡር ዶክተር አርቲስት መሐሙድ አሕመድ «ለታሪክ» የተሰኘውንና...

ሜታ ‘ፌስቡክ እና ኢንስታግራም በቀረበባቸው ክስ 18 ቢሊዮን ዶላር ለመክፈል ተስማማ

ግዙፉ የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያ ሜታ በፌስቡክ እና በኢንስታግራም ምክንያት...