ስፔናዊው አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2025/26 ውድድር ዓመት ምርጥ አሰልጣኝ ሽልማትን አሸንፏል፡፡
ሚኬል አርቴታ በውድድር ዓመቱ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ከአርሰናል ጋር ያነሳ ሲሆን በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግም ክለቡን ለፍፃሜ አድርሷል።
አርሴን ቬንገር በፈረንጆቹ 2003/4 የፕሪሚየር ሊጉ የዓመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ሽልማትን ካሸነፉ ወዲህ የአርሰናል አሰልጣኝ ሽልማቱን ሲያሸንፍ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
