ስነ ስርዓት የስልጣኔ ምልክት ነው

Date:

አልፎ ለሚሄድ መኪና አክብሮት ለማሳዬት ክንንቡን የሚያወርደው
የአገው ምድር ማህበረሰብ ስነስርአት አክባሪነት ሕግ አክባሪነት እንዲሁም ቃል አክባሪነት ላይ በባህላዊ ለዛው የታጀበ
“አንታጉ ” የተባለ በደሳለኝ መኩሪያው የተደረሰ በለይኩን ሲሳይ የተዘጋጀ ለመጀመሪያ ጊዜ በአገውኛ ቋንቋ ተሰርቶ በአማርኛ subtitle የተደረገ ፊልም በደማቅ ስነስርዓት እነ ጋሼ አያልነህ ሙላቱ እና ሌሎችም በርካታ እንግዶች በተገኙበት በሀገር ፍቅር ቴአትር መርቀናል::

ፕሮዲውሰሩ ወዳጃችን ለይኩን ሲሳይ የአዲስ አበባ ልጅ ነው::
ልክ ትምህርቱን እንደጨረሰ በመምህርነት ሥራ ምክንያት በ 1991 ዓ.ም ወደ ጎጃም አገው ምድር ይሄዳል::

በሁዋላም ለ ጥበብ ባለው ፍቅር ከሚሰራቸው ስራዎች የተነሳ አዊ ብሄረሰብ አስተደዳር ባህል እና ቱሪዝም በመሆን አገልግሏል:: አሁን የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ምክትል ቢሮ ኃላፊ ነው:: አማርኛ ኦሮምኛ ሱማሊኛ እና አገውኛ ይናገራል:: ” አታንጉ” ፊልም ፕሮዲውሰር ነው::
“አታንጉ” ማለት ” በአገውኛ ‘እንዲያ ነው እንጂ” እንደማለት ነው::

የፊልሙ ዋና መልክትም ጥንታዊ ባህል, ሕግ አክባሪነትን, ቃል ጠባቂነት, እስከምን ድረስ ሰዎች ይሄዳሉ የሚለዉን የሚያስተላልፍ ድንቅ ፊልም ነው:: ልባሙን ደራሲ ከልብ አመሰግናለሁ::

የአዊ ባህል እና ቱሪዝም, የአገው ምሁራን ማህበር ወጣቶች እና ሁሉንም በዚህ መልካም ጅምር ላይ የተሳተፋችሁ አካላት በጣም እናመሰግናለን :: በርቱልን..ከጎናችሁ ነን::

ሀገራችን የብዙ መልካም ባህሎች መገኛ በመሆኗ የሀገራችንን በጎ ጎን ውብ ባህል በማሳዬት ሌሎችንም እንደዚህ መስራት ቢቻል ለመጪው ትውልድ በዙ ትምህርት ማስተላለፍ ይቻላል::

ኢትዮጵያ እንዲህ ነች ” አንታጉ “
#Leykun Sisay

አክባሪያችሁ
ፍሬዓለም ሺባባው

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...