ሶማሊላንድ ለአሜሪካ እና ለእስራኤል የጦር ሰፈርና ማዕድን ቁፋሮ ዕድል እንደምትሰጥ አስታወቀች

Date:

ራሷን በራሷ የምታስተዳድረው ሶማሊላንድ፣ ለበርካታ አስርት ዓመታት ለምታደርገው የዓለም አቀፍ የነፃነት እውቅና ጥያቄ ድጋፍ ለማግኘት ለአሜሪካ እና ለእስራኤል ልዩ የኢንቨስትመንትና የደህንነት ጥያቄ ማቅረቧ ተሰማ።

የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ሚኒስትር ክዳር ሁሴን አብዲ ለኤኤፍፒ እንደገለጹት፣ ግዛታቸው ለአሜሪካ ልዩ የማዕድን ቁፋሮ ፈቃድ የመስጠትና የጦር ሰፈር እንዲገነባ የመፍቀድ ከፍተኛ ፍላጎት አላት።

ግዛቷ እንደ ሊቲየም እና ኮልታን ያሉ ከፍተኛ ተፈላጊነት ያላቸው ማዕድናት እንደሚገኙባት የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ለእነዚህ ሀብቶች ቅድሚያ ለአሜሪካና ለእስራኤል ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

በስትራቴጂያዊ ስፍራ ላይ የምትገኘው ሶማሊላንድ፣ አሜሪካና እስራኤል በግዛቷ ላይ ወታደራዊ መገኘት እንዲኖራቸው መፍቀዷ በየመን በኩል የሁቲ አማጽያን በቀይ ባሕርና በኤደን ባሕረ ሰላጤ ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት ለመከላከል ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል።

ይህ ጥሪ የቀረበው ባለፈው ታህሳስ ወር እስራኤል የሶማሊላንድን ነፃነት ዕውቅና መስጠቷን ተከትሎ ሲሆን፣ ሶማሊላንድ እ.ኤ.አ በ1991 ከሶማሊያ መገንጠሏን ብታውጅም እስካሁን ሰፊ ዓለም አቀፍ እውቅና አላገኘችም።

የሞቃዲሾ መንግሥት ሶማሊላንድን አሁንም እንደ አንድ የሶማሊያ አካል አድርጎ ቢመለከተውም፣ ግዛቷ ግን ላለፉት 30 ዓመታት የራሷ ፓስፖርት፣ መገበያያ ገንዘብና የጸጥታ ኃይል ያላት ራሱን የቻለ አስተዳደር ሆና እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...

የተጀመሩ የትምህርት ሪፎርሞችን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም በቁርጠኝነት መስራት ይገባል

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ...

የአዉሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የቡና ገበያ መዳረሻዎች እየፈለገ ነዉ

በፈረንጆቹ 2023 የፀደቀው የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ ህግ ምርቶች...