ቢላሉል ሐበሺ የልማትና የመረዳጃ እድር 2ኛውን የቢላል የክብር እውቅና መርሃ ግብር በሸራተን ሆቴል እያካሄደ ይገኛል።
በእውቅና መርሃ ግብሩ ላይ በአመራር፣ በንግድና ኢንቨስትመንት፣ በበጎ አድራጎት፣ በታሪክና ስነ–ፅሁፍ እንዲሁም በልዩ ተመስጋኝ ዘርፎች ለሀገር ብሎም ለወገን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ግለሰቦች እውቅና ሰጥቷል።
በታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የገንዘብ ድጋፍ፣ በበርካታ ዘርፎች የልማት ስራዎች፣ ለበርካታ ዜጎች የገንዘብ ልገሳ ብሎም ከ79 ሺህ በላይ ዜጎች የስራ እድልን መፍጠር የቻሉት ሼኽ ሙሐመድ አል አሙዲ ላበረከቱት ዘርፈ ብዙ አስተዋፅኦ የክብር እውቅና ተበርክቶላቸዋል።
ልዩ ተመስጋኝ:— ሙሐመድ አል አሙዲ
በታሪክና ስነ–ፅሁፍ ዘርፍ:– ወ/ገብርኤል አሰጌ
በአመራር ዘርፍ:– ሼኽ ሆጀሌ አል ሀሰን
በጥናትና ምርምር ዘርፍ:–
ፕሮፌሰር ጀማል አብዱልቃድር
በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍ:– ሀጂ ሙሐመድ አብዱላሂ ኦግሰዴ (ዶ/ር)
በበጎ አድራጎት ዘርፍ:–ሐጂ አዳነ ማሙዬ
በ2ኛው የቢላል የክብር እውቅና ተሸላሚ ሆነዋል።
25ኛ የምስረታ አመቱን በተለያዩ መርሃ ግብሮች እያከበረ የሚገኘው ቢላሉል ሐበሺ የልማትና መረዳጃ እድር ከእውቅና መርሃ ግብሩ ባሻገር ከ1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የሚደረግባቸውን ሶስት ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ይፋ አድርጓል።
የዛሬው መድረክ መታሰቢያነቱ ህይወታቸውን ለእስልምና መስፋፋት ለሰዉ ቀደምት ኢትዮጵያዊ አሊሞች መደረጉ ተመላክቷል።
