በልዩ መርሐ ግብር እንዲገኙ ስለ መጋበዝ

Date:


ታኅሣሥ 24 ቀን 2017 ዓ.ም.  በሕይወተ ሥጋ የተለየን አንጋፋው የግጥም እና ዜማ ደራሲ እንዲሁም ፕሮዲውሰር የነበረው ያየህ ይራድ አላምረው፥ በሕይወት ዘመኑ ያሰባሰባቸውን በዓይነትም በቁጥርም በርካታ መጻሕፍት፣ የጽሑፍ እና የሙዚቃ ኅትመት ውጤቶችን፣ ቤተሰቦቹ በስሙ ለኢትዮጵያ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) ያበረክታሉ።

ተቋሙም እነዚህን የአርቲስቱን ውድ ስብሰቦች በልዩ ኹኔታ ራሱን የቻለ በስሙ የተሰየመ የንባብ ክፍል በማዘጋጀት በልዩ ክብር ይረከባል።

ስለኾነም፥ እነዚህን ውድ የመጻሕፍት እና የኅትመት ውጤቶችን በይፋ ለመረከብ፥ረቡዕ ታኅሣሥ 22 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ፣ በኢትዮጵያ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) ዐዲሱ ሕንጻ ላይ በተዘጋጀው ልዩ የርክክብ መርኀ ግብር እርስዎም እንዲገኙልን በአክብሮት ተጋብዘዋል።

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብት እና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 9 2019 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

-የግዮን እንግዳ አምዳችን :- ‹‹ምንጩና ጸሐፊው በማይታወቅ መረጃ መመራት አደገኛ...

ሸኽ መሃመድ አል አሙዲ ተጨማሪ 40 ሺህ ሠራተኞች እንዲቀጠሩ አቅጣጫ ሰጡ

የMIDROC Investment Group ሊቀመንበር ሼክ መሃመድ ሁሴን አል...

የወርቅ ማዕድን ሠራተኛው ከመገደላቸው በፊት ቤተሰባቸው ከታጣቂዎች ጋር ያደረገው የመጨረሻው የስልክ ምልልስ

ማስጠንቀቂያ፡ ቀጥሎ የሚያነብቡት ታሪክ ሊረብሽዎት ይችላል በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ...