በትግራይ ክልል የታሪካዊው አል-ነጃሺ መስጂድ እድሳት ሥራ መጠናቀቁ ተገለጸ

Date:

በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ታሪካዊው የአል ነጃሺ መስጂድ የእድሳት ሥራ መጠናቀቁን የትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ኃይላይ በየነ ለአሐዱ እንደተናገሩት መስጂዱ ባለፉት 9 ወራት እድሳት ሲደረግለት ቆይቷል፡፡

የእድሳት ሥራውም ከቱርክ ልማት ኤጀንሲ በተገኘ ድጋፍ መከናወኑን ተናግረዋል፡፡

አክለውም “በአሁኑ ጊዜ ከመስጂዱ የተዘረፉ ቅርሶችን ቁጥር የማጣራት ሥራ እየተሰራ ነው” ሲሉ ገልጸዋል።

ይህም በግጭቱ እና በተፈጥሮ አደጋዎች ከፍተኛ ውድቀት ያጋጠመውን የትግራይን የቱሪዝም ዘርፍ ለማነቃቃት እየተካሄደ ያለው የመልሶ ማቋቋም ሰፊ እንቅስቃሴ አካል መሆኑን አመላክተዋል።

በተጨማሪም በትግራይ ክልል በጦርነትና በክረምቱ ከባድ ዝናብ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸውን በርካታ ቅርሶች የማደስና የመገንባት ሥራ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

“ከአፍሪካ ጥንታዊ እስላማዊ ቅርሶች ውስጥ አንዱ የሆነው የአል-ነጃሺ መስጂድ ጥልቅ ታሪካዊ እና ባህላዊ ጠቀሜታ አለው” ያሉት ምክትል ኃላፊው፤ “የተሃድሶው መጠናቀቅ ክልሉ ከጦርነት ውድመት እያገገመ ለመምጣቱ ማሳያ ነው” ብለዋል።

በትግራይ ክልል ከዉቅሮ 11 ኪሎሜትር ከአዲስ አበባ 800 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኘዉ አልነጃሺ መስጂድ በእስለምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠዉ ታሪካዊ መስጂድ መሆኑ ይታወቃል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...

ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት እውቅና ሰጠ

የፖርቹጋሉ ክለብ ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት ማሪያ ዶሎሬስ...

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...