የመንገድ ትራፊክ አደጋን ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት አሽከርካሪዎች ህጉን ከማክበር ባለፈ በከፍተኛ ጥንቃቄ ማሽከርከር እንዳለባቸው ተገለፀ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከካኪ ሞተርስ ጋር በመተባበር ለአገልግሎቱ አሽከርካሪዎች እየተሰጠ ባለው “የተሽከርካሪ የቴክኒክ እውቀትና የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና” ላይ ኢንስፔክተር አሰፋ መዝገቡ እንደገለፁት አሽከርካሪዎች መኪና ላይ ከመውጣታቸው በፊት የተሽከርካሪውን ደህንነት ማረጋገጥ እንዲሁም በማሽከርከር ሂደት የመንገድ ሁኔታና የትራፊክ ህጉ የሚፈቅደውና የሚከለክለውን አክብረው በከፍተኛ ጥንቃቄ በማሽከርከር ኃላፊነታቸውን መወጣት አለባቸው።
ኢንስፔክተር አሰፋ አያይዘውም አሽከርካሪዎች በየጊዜው የሚወጡ የትራፊክ ህጎችን ተከታትሎ መገንዘብ፣ በሰው ህይወትና በተቋማቸው ንብረት ላይ ከሚደርስ አደጋ ለመጠበቅ እንደሚረዳቸው አስገንዝበዋል።
