በአዲስ አበባ የእንስሳት እንቅስቃሴ እንዳይኖር ተጠናክሮ እየተሰራ ነዉ

Date:

በአዲስ አበባ ከተማ በተለይም በዋና ዋና መንገዶች ላይ የኮሪደር ልማቱን ከመጠበቅ አንፃር በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ የገለጸው የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ወደ ፊት ምንም አይነት የእንስሳት እንቅስቃሴ እንዳይኖር ለማድረግ አጠናክሮ እንደሚሰራበት አስታውቋል።

በዚህም መሠረት በአሁኑ ወቅት በከተማዋ አገልግሎት ላይ ከሚውሉ እንስሳት አንዷ የሆነችውን አህያን በተመለከተ በኮሪዶር መንገዶች ላይ መንዳት የተከለከለ መሆኑን የባለስልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ገልጸዋል።

“ዘመን እየተሻሻለ ነው ድሮ በአህያ ነበር ጭነቶቻችንን የምንጭነው አሁን ደግሞ በተሽከርካሪ ነው” ሲሉ የገለጹት ዋና ሥራ አስኪያጁ አሁን ላይ ከተሽከርካሪም ደግሞ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መምጣታቸውን አንስተዋል።

ስለዚህም ከተማ ከቴክኖሎጂ ጋር የተቀናጀ አሰራር እንጂ ወደኋላ ተመልሶ የቀሩ የትራንስፖርት አማራጮችን የሚጠቀምበት ሁኔታ እንደሌለ አፅንኦት ሰጥተዋል።

በመሆኑም በተለይም የኮሪደር ልማቱን አጠቃቀም ተከትሎ ለማህበረሰቡ በርካታ የግንዛቤ ማስጨበጫ መሰራቱን ገልጸው አውቆ የሚያጠፋ ካለ ግን የሕግ ማስከበር ሥራ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

በዚህ ሂደት ውስጥም የቅጣት ደረጃዎችን መሠረት አድርጎ የሚወሰዱ እርምጃዎች መኖራቸውን አንስተው “የሚጣለው ቅጣት ግን አቅምን ያገናዘበ ነው” ብለዋል።

(አሐዱ ሬድዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...

የብሔር ፌደራሊዝምን ለማስቀጠል “የቆረጡ” ተመካካሪዎች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 14ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች የአጀንዳ...

“የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው” ፓትርያርኩ

የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው...