በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከ104 ወንጀሎች 12ቱ ብቻ የሕግ ምላሽ አገኙ

Date:

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የመሠረተ ልማት ዝርፊያ ወንጀሎች እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ገለጸ።

በ2017 የበጀት ዓመት በአዲስ አበባና በሸገር ከተማ በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ላይ ከተፈጸሙት 104 ወንጀሎች ውስጥ የሕግ ውሳኔ ያገኙት 12ቱ ብቻ መሆናቸውን በቅርቡ በተካሄደ ከፍተኛ የአመራሮች ምክክር መድረክ ላይ በቀረበ መረጃ ተመላክቷል።

መድረኩ አገልግሎቱ ፣ የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ፣ የፌዴራል ፖሊስ እንዲሁም ከፍተኛ የፀጥታና የፍትሕ ተቋማት አመራሮችን ያሰባሰበ ሲሆን፣ የመሠረተ ልማቶችን ደህንነት የማረጋገጥ፣ የኃይል ስርቆትን የመዋጋት እና ከንብረት ጋር በተያያዙ ወንጀሎች ተጠያቂነትን የማስፈን ስትራቴጂዎችን በመቅረጽ ላይ  ትኩረት ማድረጉን ካፒታል ተመልክቷል ።

የተቋሙ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ገበየሁ ሊካሳ፣ የእነዚህ ወንጀሎች ቁጥር “በከፍተኛ ፍጥነት” እየጨመረ መሆኑን ገልጸዋል።

እነዚህ ወንጀሎች የአገልግሎቱ አስተማማኝ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ለማስፋፋት የሚያደርገውን ጥረት ከማደናቀፋቸው ባሻገር፣ የሕዝብን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉና የሀገርን ልማት የሚያደናቅፉ መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥተዋል።

የፀጥታና የፍትሕ አካላት እነዚህን ወንጀሎች በመከላከልና ወንጀለኞች ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ በማድረግ ረገድ ጥረታቸውን እንዲያጠናክሩ አሳስበዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...